ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Page 6

ዳግማዊ ምኒልክ (ርዕስ አንቀጽ) …ምን ለመሆን? ብሎ እነሱን የሚኮረኩር፣ የት ለመድረስ ?...ብሎ እነሱን በጥያቄ የሚያጣድፋቸው፣እሩጫው ወዴት ብሎ እነሱን የሚወቅሳቸው፣ የራሳቸው ሒሊናም ሆነ ሌላ ሰው የለም። በእርሱ ፋንታ በርቱ የሚል ድምጽ ግን እንደገደል ማሚቶ ከሁሉም ቦታ ይሰማል። ስንቱ ነው የእናቱንና የአባቱን መቃብር የሚጎበኘው? አልፎ አልፎስ ብቅ ብሎ የሚጠርገው? የሚንከባከበው? ምኒልክ ከሞተ አንድ መቶ አመቱ ነው። ይህን ምክንያት በማድረግ በስሙ የተዘከረበት ስሙ የተነሳበት ፣ጉባዔ በሥነስርዓቱ የተካሄደበት ጊዜ የለም። ቢኖርም ብዙበቦታ አልተሰማም። እኛ ኢትዮጵያኖች ሙታንን በማስታወስ „ዘለዓለማዊ“ ማድረግ ቀርቶ የሰባት አመቱ -ጥቂቱ ይህን ቀን ይጠብቃል- ተዝካር ሳይወጣ እንኳን አብዛኛዎቻችን እንዳልነበሩ እንረሳቸዋለን። አፈር ሰውዬው አንዴ ከለበሰ ማን አስታውሶት የእሱን መቃብር መልሶ መላልሶ ይጎበኛል? ማን አታክልት መቃብሩ ላይ ተክሎ አልፎ አልፎ እየወረደ እሱን ይኮተኩታል? አበባውንስ ጥዋት ማታ ወሃ እየቀዳ ማን ያጠጣል? ሜዳውንና አካባቢውንስ ማን ዞር ብሎ ይጠርጋል? ይህን የሙታን ቀን የሚባለውን ነገር ቤተ- ክርስቲያናችንም አታውቅም። የሞስሊሙም ማህበረ ሰቡም እንደዚሁ አያውቀውም። አይንከባከበውም። ለአገራቸው ዳር ድንበር ወይም ለነጻነታቸውና ለባንዲራቸው የሞቱትንና የወደቁትን ልጆቹዋን የመከላከያ የጦር ሠራዊቱም የጦር ኃይሉም ይህን ቀን በአመት አንዴ የሚያስታውስበት ቀን እንኳን - ሐውልት መሥራቱን እንተወው - የለውም። ያለውንና የኖረውን ማጥፋት የነበረውን ማቃጠል ከዚያም አልፎ በእሱ ቦታ ደግሞ ለአዲሱ ትውልድ „…እኔም እኮ አዲስ ታሪክ መጻፍ እችላለሁ እንችላለን“ በሚለው ከንቱ ውዳሴ ብቻ ብዙ ትርዕይቶች ማቅረቡን የፖለቲካ መደቡ በተቃራኒው ያውቅበታል። በአለፉት አመታት እነደዚህ ዓይነቱን ቲያትሮች - የተመዘገቡ ናቸው- በተደጋጋሚ አይተናል። 6 ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4 ለቴዎድሮስም፣…ለዮሐንስም፣…ለዘውዲቱም ፣ለኃይለ ሥላሴም …ለንጉሥ ….እገሌና እገሊት ….ጥቂቱን ብቻ ለመቁጠር እነቁጠር ለእነሱም -ይህ ነው የአብዛኛው አስተሳሰብ- ምንም ስለ አልተደረገ „ለምን ለምኒልክ ብቻ ይህን ይህል ቦታ ከአልጠፋ ነገር ትሰጣላችሁ ?“ የሚለን ሰው አይጠፋም። ምኒልክ የሚለው ስም በኢትዮጵያ የነገሥታትና የአገሪቱ ታሪክ -የሌሎቹ ስም ይደጋገማል - በአለፉት ሦስት ሺህ ዓመታት ምክንያቱ ምን እነደሆን በግልጽ አይታወቅም እንጂሁለት ጊዜ ብቻ ነው በታሪክ ላይ ብቅ ያለው። አንደኛው በኢትዮጵያ መንግሥትና ግዛት የም ሥረታ ሚቶሎጂ [1]፣ የቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከስንት ሺህ አመት በሁዋላ ብቅ ያለው የዳግማዊ ምኒልክ ሥራና ገድል ነው። እኛ፣ የዚህን ትልቅ ጥቁር ሰው፣ የምኒልክን ታሪክ ዛሬ የምናነሳው መቶኛውን የሙት አመት ለማስታወስ ነው። የእሳቸውን ታሪክ በጥቂቱ አስቀምጠን እንዳለፍን ምኒልክ ከሞቱ ከአምስት አመት በሁዋላ በደቡብ አፍሪካ የተወለዱት የሚስተር ኔልሰን ማንዴላ ዕረፍት - እኛም በዝግጅት ላይ እንዳለን ደርሶን- ይህ ዜና እኛንም እነደ ሌሎቹ አስደነግጦአል። በሁለቱም የአፍሪካ መሪዎች መካከል የአንድ መቶ አመት ልዩነት አለ። 7