ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Page 32

አራት ጣቢያዎችን ጠቅሰውልናል። አፍሪቃ! እንዴት ሰነበተች ? አንደኛው በልጅነት ዕድሜአቸው በጠምቄ ገዳም ያሳለፉት ጊዜና ከአስተማሪያቸው ከአባ ሸዋ ዘርፍ ያገኙት ተመክሮና ትምህርት ነው። ሁለተኛው ተማርከው በአጼ ቴዎድሮስ ችሎት እዚያ ላይ ያሳለፉት ጊዜና የቁም እሥር ዘመን ነው። ሦስተኛው አብሮአቸው ታሥረው የነበሩት የሸዋ መሣፍንቶችና መኳንንቶች „ምክር ነው።“ የመጨረሻው ትምህርት መቅደላ ላይ የተዋወቁአቸው የአውሮፓ „ምሁሮች“ ናቸው። ምኒልክ በእነዚህና በሌሎች ተመክሮች የኢትዮጵያ ነጻነት ጠብቆና አስከብሮ ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፎ ሄዶአል። „ተማረ፣አወቀ፣ነገር ገብቶታል“ የተባለው ትውልድ ደግሞ እንደምናውቀው „…በተለያዩ ፍልስፍናዎችና የአምባገነን ፖለቲካ አይዶኦሎጂዎች“ አብዶ፣ ቀላሉን …የሰበአዊና የዲሞክራሲዊ መብቶች መከበርን እንኳን፣ የነጻ-ሕብረተሰብን መመሥረትን፣ የግል ሐብትን፣ ነጻ ስብሰባና ነጻ ፕሬስን ሲቃወም ይህን በ21 ኛው ክፍለ ዘመን በአዲስ አበባና በአሥመራ ማየቱና መሰማቱ ምንድነው። በምኒልክ ላይ የትችት ናዳቸውን የሚወረውሩ ከአሉ፣ እራሳቸው በመጀመሪያ ኢትዮጵያን ከሚበትነው ከአምባገነን ከቴታሊቴሪያን አስተሳሰብ ማለቀቅ ይኖርባቸዋል። እንደዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ግን - ንጉሣዊ አገዛዝን ቀደም ሲል ፣ፈሺዝምን፣ ከእሱም ጋር ፍልስፍናው የተወለደውም እዚህ ነው- ኮምንዝምንም በደንብ በሚያውቀው በጀርመኑ አገር ስብሰባ ላይ እንደዚህ ዓይነቱ ትችት አልተሰማም። ከኔልሰን ማንዴላ ይልማ ኃይለ ሚካኤል ከዴሞክራቱ ጋር ! መቼም ስለዚህ ሰው በአለፉት ሁለትና ሦስት፣…አራትና አምስት ቀናት፣ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቀን ብቻ በዓለም ዙሪያ ታትመው የወጡትን ዕለታዊ ጋዜጣዎች እነሱን ብቻ አንድ ሰው ጠርዞ ቢያወጣው ረጅምና ብዙ ገጽ የያዘ ጥሩ መጽሓፍ ሊወጣው ይችላል። ይህ ከሆነ ለምን አሁን እንደገና ስለ ኔልሰን ማንዴላ? የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች አንዲት ጋዜጠኛ ተገርማ ከዚያ ሁና እንደዘገበቺው ስብሰባቸውን አቁመው - ይህ የትም አልታየም የትም አልተደረገም እሱዋም እንደዚህ ዓይነቱ ክብር የትም አልተሰማም ትላለች- የሕሊና ጸሎት መሞታቸው እንደተሰማ እነሱ ብድግ ብለው አድርገዋል። 32 ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4 33