ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ | Page 10

እኛም ይህን ማለቱን ለዛሬ - ይቅርታ አድርጉልን-እንመርጣለን። ምኒልክ መልካም ንባብ! መልካም ትካዜ! መልካም ግንዛቤና ምናልባት ደግሞ መልካም ጥያቄና አስተያየት ! ጀግንነትና የአዋቂ ሰው ሥራ ታሪክ እንደ ምኒልክ በዓለም ላይ የተከበረ፣ እንደ እሱም በአንዳንድ በገዛ ልጆቹ አልአግባብ የተጠላ - ሰው የለም! የዘመናዊ ፖለቲካ አሠራር አጀማማር በኢትዮጵያ ዋናው አዘጋጅ ይልማ ኃይለ ሚካኤል [1](ይህን ደግሞ በሌሎች ትላልቅ የዓለም ሕዝብ ታሪክ የምናየው ነው- ሌላው ቀርቶ በተኩላ ሞግዚትነትና ከእሱዋም „የእናት ወተት“( እርቦአት ልትበላቸው፣አውሬ ስለሆነች ትችላለች፣ ግን ታሪካቸው ላይ ይህን አላደረገችም) የእሱዋን ወተት ጠብተው ያደጉት- ይህን አልነበረም ብሎ መከራከር የአንባቢው ፋንታ ነውሁለቱ የሮም መንግሥት መሥራች ወንድማማቾች ሮሚውሲና ሮሙሎስ፣ እዚህ ላይ ይህን ማስታወሱ በቂ ነው፣…. ግሪኮችም፣ጀርመኖችም፣…ሩሲያና ቻይናዎችም ጃፓኖችም በየፊናቸው እረ ስንቱ ሥልጣኔ… ተመሣሣይ ታሪክ አሉአቸው) ዜናው ተናፍሶ ወሬው ዓለምን አዳርሶ ጥቁሩንም ነጩንም ቀዩንም ፍጡር ከዚያም ራቅ ብለው የሚኖሩትንም ቢጫውንም ሕዝብ ያኔ ከነበሩት ከእነጌቶቻቸው ያስደነገጠው አንድ ነገር ቢኖር አደዋ ነው። ትንሽ ቆይቶም ዜናው በቅኝ ግዛት መዳፍ ሥር ነጻነታቸውን ተገፈው የሚኖሩትን ያኔ „ባሪያዎች“ ተብለው የተናቁትን ሕዝቦች የልብ ልብ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስደሰተው በሁዋላም እንደምናነበው የታሪክ ጸሓፊዎችንም በብዙ ቦታ በጣም ያስገረመው የአደዋ ጦርነት፣ የተጀመረው በየካቲት 23 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም. ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ ነው። በዚህ በትክክል በስንት ሰዓት በሚለው ጥያቄ ላይ የተለያዩ ግምቶችና ማስረጃዎች -ከተለያዩ ሰዎች ይቀርባሉ። 10 ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4 11