ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 9

እኛ የምንተቸውና የምንቃወመው፣መስተካከል አለበት የምንለው ጉዳይ ቢኖር„የራስንና የግል ወታደሮችን ሰብስበው አደራጅተው አስታጥቀው በጠበንጃ አፈ ሙዝ አስገድደው …እኛ ብቻ ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን ነገር እናውቃለን እናንተ አርፋችሁ ተቀመጡ…“ የሚሉትን የአሥራ ዘጠነኛውና የሃኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎችን ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ ደግሞ አሁን በያዝነው በ21ኛ ክፍለ-ዘመን የትም አገር ምንም ቦታ በሥራ ተተርጉሞ ወጤት ያመጣ ሥርዓት አይደለም። ይህንንም ጉዳይ ለማሳየት ጀርመኖቹን እንደ ምሳሌ ወስደን ከብዙ በጥቂቱ በዚህ ሕትመታችን -ዘለቅ ስትሉ ታገኙታላችሁ – አንስተነዋል። እንደሚታወቀው የጀርመን ፋሽሽቶችና የጀርመን ኮሚኒስቶች የእራሳቸውን ሰዎች ሰብስበው የወታደር ልብስ አልብሰው የራሳቸውን የስለላ ድርጅት ዘርግተው የቅስቀሳና የፕሮፓጋንዳ ክፍል ከፍተው፣ በመንግሥት ሥር የራሳቸውን „መንግሥት „ መሥርተው ይህችን አገር አተረማምሰዋል። የዘር እና የመደብ ጥላቻ ትምህርትና ቲዎሪ -ፋሺዝምም ሆነ ኮሚኒዚምእነዚህ ዓለምን ያተረማመሱ ሁለቱ አይዲኦሎጂዎች የበቀሉት ቀስ ብለውም ዓለምን ያዳረሱት ከዚሁ ከጀርመን አገር :- ከሒትለርና ከማርክስ ብዕር፣ ከእነሱም ጭንቅላት ወጥተው ነው። እነሱን አባረው ደግሞ እላይ ገና ከመጀመሪያው እንዳልነው ይኸው ነጻው የጀርመን ሕዝብ ንጹሁን የዲሞክራሲ አየር እተነፈሰ ጋዜጣውንና መጽሓፉን እየጻፈ ድርሰቱን እየደረሰ ምርምሩን በነጻነት እያካሄደ ቲያትሩን እየተጫወተ ፊልሙን እየቀረጸ በዓለም ላይ ምን የመሰለ ምርጥ የእንዱስትሪ ዕቃዎ