ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 6

የአለፈው ሃምሣ አመት ታሪካችን ትውልዱ ለምን በከንቱ በዚህ ጉዳይ ላይ አሳለፈ? ብሎም በተዘዋዋሪ ይጠይቃል። „ትግል“ የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም አለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ቀስ ብሎ እየተንሸራተተ የገባው ይህ „የብሔርና የመደብ ትግል“ ቃል (መንግሥቱ ኃይለማሪያም „ጥሩ“ አድረጎ „በከርሰ መቃብራቸው ላይ እንቀመጣለን „ ብሎ አስቀምጦታል) ገፍትሮ አሁንም ቢሆን የት እንደከተተን በዓይናችን ጥዋት ማታ እናያለን።ከሩቅም ሆነን እንሰማለንም። እሱንም አንስተን እዚያና እዚህ ነስንሰን – ወረድ ብላችሁ እንደምትመለከቱት እናልፋለን። እንግዲህ ለዚህም ነው ይህን ጉዳይ ግልጽ ለማድረግ የውሾችን ታሪክ መርጠንም ያስቀደምነው። የአንበሳ ወይም የነብሮች ወይም ደግሞ የድመቶች ታሪክ ልንለውም እነችላለን። ይህን ያህል „ልዪነት“ የላቸውምአንድ ናቸው። ውሻ ግን ከነብር ታማኝ ነው። ንቁ ነው። ውሻ ከአስተማሩት -እስከ መቶ የተለያዩ ቃላቶችን መያዝ ይችላል። እነሱንም አቀነባብሮ ምን እንደ ተባለ መላ መምታትም ይችልበታል። በዚህም የሚሰማቸውን ነገሮች አዳምጦ-ትዕዛዝ ይቀበላል። እንደምናውቀው ደግሞ በጋራ የሚኖሩና አጥቂ፣ አውሬ ሲመጣባቸው ለጋራም ጩኸት የሚተባበሩ ናቸው። በዚያው መጠን አጥንት ከአዩ የሚቦጫጨቁምእነሱውናቸው። ርዕዮተ-ዓለም ወይስ እሴት ? ከማለት ይልቅ „አይዲኦሎጂ ወይስ ትሩፋት/ ቨርቺውስ?“ ብለን እሱን ማስቀድምና መመልከት ምርጫችን በሆነ ነበር። „ስለህሊና ስለልቦና ስለ ፍቅር ስለ ርህሩህነት ስለ መከባበር ስለ ተግሳጽና ምክር …“ ስለነዚህ ሁሉ ለማንሳትና ታሪክና ምሳሌን ተደግፎ ለማብራራት የሚፈልግ ሰው ቨርቺውስ/ትሩፋት ውስጥገብቶ ዋኝቶ ከዚያ ወጥቶ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ሰብስቦ ለማሳየት ከዚህ የበለጠ ሜዳ የትም እሱ አያገኝም። 6