ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 59

ቀኃሥና ማርቲን ሉተር ኪንግ ስድሣው አመተ ምህረት የእኩልነትጥያቄ ዘመን ነበር። በ1969 (እ.አ.አ.) የሰብዓዊ መብት ታጋዩ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በዘረኞቹ "በነጭ ዘር በላይነት" በሚያምኑ ነፍስ ገዳዮች የተገደለበት ዓመትም ነበር። የማርቲን ሉተር ኪንግ ጥያቄ "...የመገንጠል" ሳይሆን የነጮችና የጥቁር ዘሮች የእኩልነት ጥያቄ ነበር። በዚያን ዘመን ለማስታወስ በአገራችን በኢትጵያ ወጣቱ ትውልድ በብዙዎቹ ዘንድ ያኔ ማንነቱ ምን እንደሆነ እንደ አሁኑ ዘመን በግልጽ በአልታወቀው አይዶሎጂ ተሳከረው ከእኩልነት አልፎ የሚሄደውን "...የመገንጠል" ጥያቄም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ "ኢትዮጵያ የሚባል ነገር የለም ብለው" በስታሊን ስም ተነስተው አሁን ያለንበት ሁኔታ ውስጥ ሳያመዛዝኑ እነሱ ከተውን ሄደዋል። 59