ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 58

ወረድ ብለው አሳቢ እናትም ፖለቲከኛም መሆናቸውን እቴጌይቱ በደንብ – በዘመኑ በነበረው አነጋገር ግልጽ አድርገዋል። „…እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያም ይሁን ብላ መጥታለችና አደራችሁን በምኑም በምኑም ነገር እንዳታሰቀይሟት። እንግዲህ ሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከችብኝ እንደሆነ እንናንተንም እጠላችኋለሁ። እኔንም እንዳታስቀይሙኝ።“ ከዚህ ዓረፍተ ነገር ቀደም ሲል ስለ ዕርዳታ ገንዘብ ጉዳይ አንሰተዋል። „…ይህን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድ ከቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ (…ነው) እንጂ ገንዘብ ተርፎን አይደለም።“ በአጭሩ „ …፩ነታችሁ እንዲጸና ብለን ነው እንጂ ገንዘብ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።“ የሚለው አረፍተ ነገር ትልቅ ትምህርት አሁንም ቢሆን ከአንድ መቶ አመት በሁዋላ የሚሰጥ ቃል ነው። እሱንም ብቻውን አላሰቀመጡትም። „ተስማሙ ተፋቀሩ“ አለበለዚያ….የሚለውን መልዕክት እቴጌይተዋ ጮክ ሳይሉ አብረው ሰደዋል። „ስምምነት፤ ፩ ድነት፣ ፍቅርና ሃይማኖት … በሰው ፊትም ኢትዮጵያኖች መሣቂያ አለመሆንና ተቸግሮም የሰው ፊት (ልመና ማለት ነው) አለማየት „ አገሪቱ የተገነባችበት የቆየ ትሩፋት /ቨርቺውስ ናቸው። መረዳት ለሚፈልግሰው የደብዳቤው መልዕክት ግልጽ ነው። የጣይቱን ደብዳቤ ጊዜ እንዳነሳው፣ „አንድነትን „ የማይፈልጉትን ሰዎች አንድ ቀን ታሪክ አንስቶ እነሱን ይወቅሳቸዋል። በተለይ „፩ነታችን እንዳይጸና- የኢትዮጵያ „ የሚፈልጉትን ኃይሎች ጊዜ ሳይረሳቸው ይፋረዳቸዋል። እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሜዳውን ይዘው የነበሩ ሰዎች „የልዩነት ቆጣሪዎች“ ነበሩ አሁን ደግሞ ዘመኑ ጊዜውም „የኢትዮጵያና የአፍሪካ አንድነት“ ፈላጊዎች ነው። ደብዳቤው መነበብ ብቻ ሳይሆን መሠራጨትም ያለበት ነው። ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6 58