ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 56

ወደፊት „በባዕድ ፊት መሳቂያና መሳለቂያ“ እንደይሆኑም ምክርና ተግሣጽ ይኸው ደብዳቤ ይሰነዝራል። የተለያዩና የተበጣበጡ የኢትዮጵያ ልጆችንም ያስጠነቅቃል። ፩ ነታችሁን አጽኑም …ይላል። የተጻፈው ከመቶ አመት በፊት ነው። የተላከውም ከሺህ ሰምንት መቶ አመት በፊት ጅምሮ ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ለምስታተዳድረው ገዳም ኑዋሪዎች ነው። „…እናንተ ብትስማሙ እርስ በእርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል …“ የሚለው ደብዳቤው ላይ የሰፈረው የዓረፍተ ነገር አሰካክ የሐዋሪያው ጳውሎስን መልዕክት -አንድ አንባቢን ያስታውሳል። ይህም እቴጌይቱ አርቀው የሚያስቡ የስው ልጆች ባህሪና የሰው ልጆች የተፈጥሮ ድክመት የት ላይ እንደሆነ አንዴትም መታረም እነደ አለበት ደህና አድረጎ የገባቸው መሆኑን ከደብዳቤው መልዕክት መገንዘብምይችላል። እቴጌይቱ ከባለቤታቸው ከአጼ ምኒልክ ጋር ጥሩ የፖለቲካ ቀያሽ (ስታረተጂስት) መሆናቸው አደዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም መስክ ላይ ደህና አድርገው በጊዜአቸው ማን መሆናቸውን አሳይተው አስመስክረዋል። ። እቴጌ ጣይቱ እንደ አጼ ምኒልክ-ብዙዎቹ እንደሚሉት-የሰው ምክር አዳምጠውም መርምረው አመዛዝነው ውሳኔ መስጠትም ይችሉበታል። „…አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል እንጂ… „ -ይህ ነው መልዕክቱን ከመቶ አመት በሁዋላ አሁን እንደገና ትኩስ አድርጎ እኛም እንድናነሳው ያደረገን አዲስ የሚያደርገውም- „…ትግሬ የብቻ ነው ሸዋ የብቻ ነው ቢገምድር ጎጃም የብቻ ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ።…