ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 51

„አል- ኑር“ የሚባል አንድ በሕግ የተመዘገበ የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች ማህበር ይህን ሕንጻ ገዝቶ ወደ መስጊድ ለመቀየር ሓሳቡን ግልጽ ከአደረገ ወዲህ ኃይለኛ ክርክር ተነስቶ ደጋፊውንም ተቃዋሚውንም አነጋግሮ „…ለምን ይህ ይሆናል? ….ለምን መሆን የለበትም?“ ወደሚለው ጥያቄ ሻጮቹንም አማኞቹንም ሰውንም ሁሉ ወደዚያ ወስዶአቸዋል። „…እንዴት መስቀልን በግማሽ ጨረቃ እንለውጣለን? እነዴትስ ዓናችን እያየ ወደዚያ ይለወጣል?“ አንዳዶቹ ሲሉ „…ከዳንኪራና ከመሸታ ቤት መስጊድ ቢሆን ይሻላል።“ የሚል መልስም ከአንዳንዶቹ እንደዚህ ሲባል ተሰምቶአል። „…ዘመናዊሥልጣኔና አጉል የሃይማኖት ንቀት ይህን አምጥቶ ሜዳውን ለሞስሊሞቹ አመቻችቶ ሰጠ „ ብለው ሌሎቹ አማረው ተናግረዋል። „በምንም ዓይነት መሽጥ የለበትም።ሁለቱ ሃይማኖቶች ካቶሊክና ኢቫንጀሊስቶቹ አንድ ላይ ቆመው ይህን ነገር ማገድ አለባቸው። „ ብለው አንድንድ ቀሳውስቶች ተነስተዋል። ግን የሁለቱ አንዴ ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ ቤተ ክርስቲያኖች ስምምነት „አንድ ለመሆን“ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል። ይህ ሁሉ የሆነው „…ብዙ ቤተ-ክርስቲያኖች በስድሳውና በሰባው አመተ ምህረት አለ ፕላን በመሰራታቸው ነው …“የሚሉም ሰዎች ድምጽ ሓምቡርግ ላይ ተሰምቶአል። ችግሩ ያለው እሱ ላይ ሳይሆን ብዙው ወጣት ትውልድ ከቤተክርስቲያን በመራቁ ነው። ወጣ ወረደ ገዢዋቹ የሞስሊም ማህበረሰብ መስጊድ አድርገን እንሰግድበታለን“ብለዋል። „…ውስጡን አድሰን 51