ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 49

አሁን ግን ሰውን ሁሉ ግራ እያጋባ የመጣው በሰሜን ጀርመን ትላልቅ ከተማዎች እንደ በረሊንና እንደ ሓምቡርግ እንዲሁም በዝቅተኛው ሳክሶኒያ ማለት በአብዛኛው ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማኞች መካከል እንደ ኮሚኒስቶቹ እዚህ መንግሥት ጫናውን በማያሳይበት አገር የምዕመናኑ ቁጥር ቀንሶ ቤተክርስቲያን እስከ መዝጋት ድረስ ያደረሰው ጉዳይ ምን እንደሆነ እሱን ለመረዳት ብዙ ሰው ግራ ተጋብቶታል። በደቡቡ ጀርመን በካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ፈጽሞ እዚያ አካባቢ አይታይም። ካቶሊኮች ኃይለኛ ሥርዓትና የጠበቀ እምነት እንዳላቸው ይነገርላቸው። ወላጆችም ባህሉን ሥነሥርዓቱን ወጉን ትውፈቱን የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናቱንና ሳምንታዊ ትምህርቱን ለልጆቻቸው ተቆጣጥረውና ጠብቀው ለእነሱ እንደተላለፈው እነሱም ማስተላለፉን-እዚህ እንደሚባለውይችሉበታል። የሉተር