ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 47

ቤተ-ክርስቲያን ሲሸጥ ሲለወጥ! ዘመኑ ተቀይሮአል። ተቀርጾ አንድ ቀን በዜና መልክ በቴሌቭዠን የተላለፈው ፊልም ከአእምሮ በቀላሉ አይጠፋም። ያኔ የተጀመረውም ጉዞ በፈጣን እርምጃ አሁን ወደፊት ቀጥሎአል። በጸሎት ሥነ-ስርዓት ነበር ያ መቅደስ ለመጨረሻ ጊዜ የተዘጋው።በርካታ ጋዜጠኞችም ታሪኩን አጅበውታል። ብዙዎቹ ደንግጠው አስተያታቸውን ሰጥተውበታል። አቴስቶቹ ምንም ነገር እንዳልሆነ በአጠገቡ አልፈዋል። ከመዘጋቱ በፊት ቀሳውስቶቹ የእሁድ ጥዋት ተሰብሰበው እንደተለመደው የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል። ምዕመናን ሥጋ ወደሙ ለመጨረሻ ጊዜ ተቀብለዋል። መዝሙር ሁሉም አብረው ዘምረዋል። ከዚያ በሁዋላ ተራ በተራ እና አንድ በአንድ ቀስ እያሉ የቤተ ክርሰተያኑን መስቀሎች ሥዕሎች መጽሓፍትና ውድ የስጦታ ዕቃዎች ዋንጫና የቄሶች ልብሶች ካባና የሻማ መስቀመጫዎችን እየተሸከሙ አውጥተው መኪና ላይ እየዘመሩ ጭነው ወደ ቤታቸው በሩን ዘግተው ተመልሰዋል። እዚያ የቀረው የሕጻናት መጠመቂያ አሸንዳና አግዳሚ ወንበሮቹ ብቻ ናቸው። በዚያን ቀን ሆነ በሌሎች የጸሎት ቀናት ያለፉት አመታት በተከታታይ አንድም ልጅ አልተጠመቀበትም። ችግሩ ያለውም እዚያ ላይ ነው። 47