ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 45

በሺህና ሁለት ሦስት ሺህ የሚቆጠሩ ብሔር /ብሔረ ሰቦች አብረው አንድ ላይ ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ቢገነጠሉና ቢገነጣጠሉ በተለይ በአፍሪካ – እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛነሽ እንደሚባለው እራሳቸውን፣ በመድሓኒትና በልብስ ….ወታደሮቻቸውን ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አስተማሪዎችን ……እነዚህን ሁሉ የሚያስተዳድሩበት የቀለብ ገንዘብ የሌላቸው- አለ የውጭ ዕርዳታ- አንድ ቀን ብቻቸውን መቆም የማይችሉ አገሮች መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ነገ ተበታትነው ሦስት ሺህ መንግሥታት መሥርተው መጥተው የእህል መግዣ ብርና የምንኖርበትየዕርዳታ ገንዘብስጡን ብለው ቢለምኑም (እንደምናውቃው ሁሉም ደሃ ነው) ከእንዱስትሪ አገሮች ውስጥ እነሱን ዞር ብሎ የሚያያቸውና እጁን የሚዘረጋላቸው ቢቆጠሩ „ትንሽ“ ናቸው። ኤርትራ እንድትገነጠልም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም የተጻፈው ደብዳቤም አንድ ቀን የሚያጠያይቅ ነው። የብሔር እኩልነት ጥያቄ እንደ ሃይማኖት እኩልነት ጥያቄ ተገቢ ጥያቄና መልስ ማግኘት ያለበትም የዲሞክራቲክ ጥያቄ ነው። ግን ለምንድነው የብሔር ጥያቄን የሚያነሱ „ነጻ-አውጪ“ ነን ብለው እራሳቸውን የሚጠሩ ድርጅት መሪዎችና ደጋፊዎች ስለ ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ጉዳይ ጮክ ብለው ሲናገሩ ሲጽፉ ሲቀሰቅሱ የማይታየው የማይሰማው?ወይም በኤርትራና በኢትዮጵያ ሁለቱም ነጻ-አውጪዎች ናቸው- ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው የማናየው? ለምንድነው „አማራ አማራ…ጨቆነን „ ይሉ የነበሩ ሰዎች አሁን በይፋ ስለ ሰበአዊ መብቶች መከበር በኢትዮጵያ በይፋ የማይናገሩት? ትልቁ ጥያቄ እሱ ነው። 45