ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 41

ተጠቅመውበታል። አፍሪካም በቀላሉ በኃያላን መንግሥታት በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን የተያዘቺውም በዚሁ በዘርና በነገድ ከፋፍሎ እና ነጥሎ ተራ በተራ በማጋጨት በተወሰደው ብልሃትና መንገድ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመያዝ የሞከረቺውና ባህረ-ነጋሽ ይባል የነበረውን የሰሜን አካባቢ „ኤርትራ“ ብላ በኁዋላ የያዘቺው በዚሁ ዘዴ ነው። በመጀመሪያ አሰብ ገዛች። በሁዋላ ምጽዋን ያዘች። ቀጥሎ አሥመራን … እንዲያውም ከዚያው ከእነሱ ሰዎች ወታደር መልምላ አስታጥቃ ኢትዮጵያን -ምኒልክ ቀድማአቸው እንጂእንዲወጉም ያደረገችውም በዚሁ ቲዎሪ ነው። „በልዩነት ጥያቄ“ በአጭሩ በዘርና በቋንቋ ልዩነት፣ በሃይማኖትና በጾታ፣ በቀለምና በቆዳ ፣ ሩዋንዳ እንደ ታየው …በአፍንጫ ልዩነት…አንድን ሕዝብ ያውም ለብዙ መቶ አመታት በሰላም የኖረን ሕዝብ ከውስጥ ገብቶ እንደ ቦንብ የዘር ጥያቄን አፈንድቶ እነሱን የሚሰማ ከተገኘ መበተን ይቻላል። መንግሥታትና ሕዝቦች ደግሞ በዚህ ጥያቄ ሳቢያብዙ ቦታ ተበትነዋል። እነ ሌኒንና እነስታሊን ደጋፊዎቻቸውን ሲያባብሉና ሕዝቡን ሲሸነግሉ ይህን ነገር „በሁለት ፍቅራቸውን በጨረሱ በተሰላቹ በባልና በሚስት ፍቺ“ በእነሱ ሁኔታ ነገሩን አስቀምጠው በዘመናቸው ምንም አትሆኑም ብትፈልጉ ትታረቃላችሁ ከአልሆነም…ትለያያላችሁ እያሉ „ግሩምና ጥሩ ትምህርት“ – መርዝ ብንለው ይሻላል – ሰጥተው የሩሲያን ሕዝብ አዋክበዋል። 41