ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 40

ከየት መጣ? ማን ነው የዚህ ጥያቄ አባቱ? የብሔር እኩልነት …እሰከ መገንጠል ድረስ አልፍሬድ ሮዝንበርግ የሒትለር ችፍ አይዲኦሊጂስት -ይህ ነበር ማዕርጉሶቭየት ኅብረትንና ምሥራቅ አውሮፓን ለመበተንና በቀላሉ ለመያዝ ከአወጣቸው እቅዶች ውስጥ አንዱ ያን የሰማይ ስባሪ የሚክለውን „ትልቁን አህጉር“ ከውስጥ ገብቶ ለመበተን ያለው አማራጭ „ሕዝቡን በዘርና በየብሔሩ ከፋፍሎ“ በኮሚኒስቶቹ በነእስታሊን ላይ እንዲነሳ ማድረግ ነው። ከእሱም ጋር „የሃይማኖትን ልዩነት አብሮ አዳምቆ መወርወር ነው።“ በስታሊን ላይ ፋሺሽቶቹ የጠነሰሱትን ተንኮልና ሤራ እነሌኒንና እነስታሊን በሩሲያ ቄሣር በዘውድ አገዛዙ ላይ ከሠላሣ አምስት አመት በፊት ቃል በቃል እነሱ ከነደፉት ፕላን ጋር አንድና ልዩነት የሌለው ኩታ ገጠም ነው። ተመሳሳይ ድርጊት ቀይሰውሁለቱ ሞገደኞች በዘመናቸው በሕዝቡ መካከል አሠራጭተዋል። ፕላኑ አንድ ነው። አላማቸው አንደኛው ፋሺዝምን ሌላው የኮሚኒስቶችን አምባገነን ሥርዓት በመሆኑ „የተለያዩ“ ናቸው። ውጤቱ ግን ዞሮ ዞሮ የሥልጣን ጉዳይ ስለሆነያውና አንድ ነው ። ሁለቱም የፈለጉት የሁዋላ ሁዋላ „አምባገነን ሥርዓታቸውን“ በተለያዩ ስሞች በሰው ልጆች ላይ ለመዘርጋት ነው። በሒትለር ወይም በስታሊን ትዕዛዝ የሚተኮሰው የፋሺሺቱ ወይም የኮሚኒስቱ ጥይት የሚገድለው ሰው ወይም ተቃዋሚዎቹ የሚታሰሩበት የእሥር ቤት ሁኔታ አንድ ነው።ያኛው ፍራሽ ላይ ሲያስተኛ ይህኛው እስረኛውን መሬት ላይ ጥሎት አይሄድም። ቅቤ ሁለቱም ለተቃዋሚዎቻቸው አያቀብሉም። ሌኒንና ስታሊን ያሰቡትን የኦስትሪያ መንግሥት በባልካን፣ ታለቁዋ ብርታኒያ ደግሞ በዘመኑዋ በቅኝ ግዛቶቹዋ ላይ በደንብ 40