ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 39

እንግዲህ በዚሁ ወደ ተነሳንበት፣ በአለፉት ሃምሳ አመታት ትልቁን ቦታ ይዘው ስለነበሩት ጥያቄዎች እንመለስ። የመደብ ትግል /የብሔር ትግል ለአርባና ሃምሣ አመታት እንዲያውም ለአለፉት ስድሳ አመታት በተከታታይ እንደ ወሃ መውቀጥ በየጊዜው (ሌላ አማራጭ መፍትሔ የሚሰጡ ቲዎሪና ትምህርቶች በዓለም ላይ የሌሉ ይመስል) መልሰው መላልሰው የኢትዮጵያ „ፖለቲከኞች“ ያንኑ „ የመደብ ወይም ደግሞእሱ አላዋጣ ሲል የብሔር ትግል“ የሚባለውን መፈክር ሲወቅጡልን ከርመዋል። በአገራችን አነጋገር የነገር ቋንጣ የለውም ይባላል። እንደ ሌላው የሠለጠኑ ሕዝቦችና መንግሥታት ከጊዜው ጋር አብረን እየተራመድን እኛም ለአለንበትና ለገባንበት ችግሮች መፍትሔ እየሰጠን እንሂድ ከአልን ከረጅም አመታት ጀምሮ የተከፈቱት አንዳንድ አጀንዳዎች ተዘግተው ወደፊት መራመድ ይኖርብናል። ተንዛዛ እኮ ! ከዚህ ሌላ ምንም የሚታወቅ መፈክር የለም እንዴ! „…አንዴ መገንጠል ሌላ ጊዜ አለመገንጠል። አንዴ „ለዲሞክራሲ ሌላ ጊዜ እዚያ ላይ ለመድረስ ጊዜ