ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 37

ይህን ለማለት በቂ ምክንያት አለን። አንዳቸውም ቢሆኑ በገዛ ቤታቸው ጋዜጠኞችን ጠርተው በይፋ ከሌሎቹ ጋር ተወዳድረው በአባሎቹ በብዙሃኑ ድምጽ የተመረጡ ሕጋዊ ማንዴት ያላቸው የድርጅት መሪዎች አይደሉም። ለምን ሰለእሱ አንስተው ሰዎች አይከራከሩም? ሁለተኛ እንዲያው በዘልማድ „…እሰከ መገንጠል ድረስ „ ይባላል እንጂ ያንን ጥያቄ በተግባር በሥራ ለመተርጎም በሚደረገው ጉዞ „የሚወራረደው ሒሳብ“ ማለት ከመስዋዕትነት እሰከ ጥፋትና ፍጅት ከዚያም አልፎ በደርግ እና በእህአዴግ የግዛት ዘመን በኤርትራ ላይ እንዳየነው ያ ሁሉ ትርምስ በመጨረሻው ወዴት ያመራል የሚለው ጥያቄ በደንብ የታሰበበት -ከላይኛውም መራራ ጉዞ ትምህርት ያልተገኘበት ታሪክ ነው። ለምን ስለዚህ ጉዳይ አይነሳም? በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው የተካለሰው ቤተ ሰብ ምን ይሆናል? እነዚህንና