ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 36

አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ „ታሪክ“ ቢያንስ በሌሎቹ ሒሳብ አርባ ሺህ ሲደርስ አንዳንዶቹም ጠበብቶች ቢያንስ „የአሥር ሺህ አመት ዕድሜ አላት“ ብለው ለማሳመን ተነስተዋል። ለቀስቃሽ ፖለቲከኞች ሳይሆን ለምን ጉዳዩን ለታሪክ ጸሓፊዎች አንተውም። ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎ የታሪክ ሰው እንዳልሆኑ እናውቃለን። „ኢትዮጵያኖች ተጋብተው ተዋልደው ተካልሰዋል ወይስ ሳይነካኩ በጉርብትና ብቻ ከሩቁ እየተያዩ ሳይካለሱ ኑረዋል ወይ?“ የሚለው ጥያቄ ወደፊት አራተኛውን ቦታ ይይዛል። የጋራ መገበያያና መግባቢያ መማሪያም ቋንቋ ሊንጉዋ ፍራንካ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚለውም ጥያቄ አብሮ ወደፊት ይታያል። ይህም አምስተኛውን ቦታ ይዞአል። በስድስተኛ ደረጃ ደግሞ ደጋግሞ እንደ አዲስ ነገር ስለ ዜጎች መብት (በዘር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን) ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያው ግለሰብ መብት መከበርና መጠበቅ በኢትዮጵያ እንደዚሁ እናነሳለን። እንግዲህ በሰባተኛ ደረጃ ስለ „ዲሞክራሲና ስለ ዲሞክራሲ የምርጫ ሥርዓት „ ስለ እነሱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜም ባይባልም፣ ቢያንስ ግልጽነት ሰፍኖ„ የወሃ ቅዳ የወሃ መልስ“ ጨዋታና ፌዝ በአገራችን ፖለቲከኞች መካከል ማሳረጊያውን እንዲያገኝ – ማሲቲካም ታኝኮ የዚያኑ ቀን ይጣላል- ይህ እንዲሆን ወደፊት ጥረት እናደርጋለን። „ለመሆኑ በድርጅቱ አመራር ውስጥ ማነው ከሌሎቹ እጩዎች ጋር በይፋ ተወዳድሮ በአባለቶቹ በድምጽ ብልጫ የተመረጠው?“ብለንም ሁሉንም ፓርቲ እንጠይቃለን። ስለብሔር እኩልነት እሰከ መገንጠል ድረስ የሚለውን ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች እዚያ ላይ ከመድረሳችሁ በፊት በእራሳችሁ ቤት በመጀመሪያ በእኩልነት ደረጃ ከሌሎች አባሎች ጋር አብራችሁ ቆማችሁ በድርጅታችሁ ውስጥ ምርጫ አካሁዳችሁ ተመረጡ እንላለን።እንደዚህ ዓይነቱን አሰራር በእያንዳንዱ ድርጅት ውስጥ መኖር አለበት ብለንም ይህን የድርጅት ውስጥ ዲሞክራሲ እናነሳለን። 36