ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 33

ከ -ካሲዮጵያ እስከ መገነጣጠል ! ከ – ካሲዮጵ ያ እስከ መ ገ ነ ጣ ጠ ል/[1] ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እንደ ማስቲካ መልሰው መላልሰው የሚታኘኩ አርዕስቶች አሉ። ይህ ደግሞ ዛሬ አይደለም የተጀመረው። ቆይቶአል። እንዲያውም የሺህ አመታት ዕድሜ አለው። አረቦች ሃይማኖትን ሰበብ አድርገው ይህቺን አገር በትነው ለመያዝ በተዳጋጋሚ ሞክረዋል። ግብጾች ከጥንት ከፈርኦን ዘመናት ጀምረው ያካሄዱት ተንኮል አንዴም ሳይሳካላቸው ቀርቶአል። ፋርስ ብዙ ደክማለች።ግን አልሆነላትም። ታላቁ እስክንድር ብቻ ነው ዓለምን ለመግዛት ሲነሳ እኛን ሳይነካን አክብሮ በድንበሩዋ ላይ በማለፉ „ቅዱስ“ የሚባለውን ስም እሱ ብቻ ሊያተርፍ የቻለው። 33