ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 30

ካሲዮጵያና የ “ካሲዮጵያ ማህደር“ በግሪኮች ታሪከ፥ንግርት/ሚቶሎጊ እቴጌ ካሲዮጵያ የኢትዮጵያው መስፍንና ንጉሥ የንጉሡ የኬፊዎስ ሚስት ናት። ከሁለቱም ትዳር ቤት አንዲት መልከ መልካም ውብ የሆነች ልጃቸው ልዕልት አንድሮሜዳ የሚባለውን ስም የያዘች ትወለዳለች።ልጅቱዋ ተወዳዳሪ የሌላት ቆንጆ ናት ይባልላታል። ያም ሆኖ በቁንጅና እና በውበት በቁመናዋና በደም ግባቱዋ ግን በዚያች በኢትዮጵያ ምድር እናትዮዋን እቴጌ ካሲዮጵያ ማንም የሚበልጥ የለም በዚያን ዘመን አብሮ ይባላል። እቴጌይቱም ይህን ስለምታውቅ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ላይ እኔን የሚበልጥ የለም ብላ የምትኩራራ ነበረች። እንዲያውም ከምድር አልፎ ማንም ቢሆን ከባህር ውስጥ ሆነ ወይም ከየትኛውም ትልቅ ውቅያኖስ በሰማይ ላይም ውብ ተፈልጎ ቢመጣ ከእኔ ጋር የሚስተካከል ማንም የለም ባይ ናት። ቆንጆ ነኝ ብላ በዚያን ዘመን የምትኮራው ሌላ መልከ መልካም ውብ ልጅ ከውቅያኖሱ ንጕሥ ከኔሮይስ የምትወለደውን ልዕልት ኔርአይደን ነበረች። ይህች ልዕልት እቴጌ ካሲዮጵያ አንዴ አደባባይ ላይ ለሰው ሁሉ በይፋ የተናገረቺውን ነገር አሳዝኖአት ለአባቱዋአፈ-ታሪኩ እንደሚለው - ዝም ብለህ ታያለህ ወይ ብላ አልቅሳ ታጫውተዋለች። አባቱዋም ተበሰጭቶ ፖሳይዶን ለሚባለው አምላክ ጉዳዩን አይቶ እንዲፋረደው አቤቱታውን ለንጉሡ አንድ ቀን ያቀርብለታል። ፖሳይዶን የአባትና ልጅ አዘኔታ ሰምቶ የባህር አሣነባሪዎችንና ዘንዶዎችን ልኮ ምድሩንና አካባቢውን በወሃ ጥፋት አንዴ ይመታውና ድብልቅልቁን ያወጣዋል።አገሪቱ የምትተርፈው ሕዝቡም ከወረደበት ማዓት አምልጦ ሰላም የሚያገኘው -ንግርት ተናጋሪዎችና ሕልም ፈቺዎች ያኔ እንዳሉት- የእቴጌ ካሲዮጵያና የኢትዮጵያው ንጉሥ 30