ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 27

…ሃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት የግል እንደሆነ፣ በዚያውም በንግድ ላይ መሰማራትና በኢኮኖሚ ዘርፍ ውስጥ ገብቶ መንቀስቃስ፣ በአካባቢና በአገር ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት…ተዘዋዎሮ ሐሳብ በጋራ ጉዳይ ላይ ከሌሎቹ ጋር መለዋወጥና መነጋገር፣ መረዳዳትና መከባበር… ሕገ መንግሥቱ እነዚህን ሁሉ እሴቶች ያረጋግጣል። የተመረጠው መንግሥትም አስተዳደርም ኃላፊነትና ግዳጅ እንዳለበትም ያነሳል።…. ሕጉን ለማክበር የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅ አገሪቱን ከአስከፊና አደገኛ ነገሮች ለመጠበቅ፣ ትምህርትንና ዕውቀትን ለማስፋፋት ሰላምን ለማውረድ ተፈጥሮን ለመጠበቅና ለመንከባከብ…ባህልናና ትውፈትን /ትራዲሽን ቋንቋንና ቅርሳቅርሶችን ለማዳበር ለመጠበቅ እንደዚሁ መንግሥትም ሕዝብም ኃላፊነት እንደአለባቸው ይገልጻል። ከዚሁ ጋር ማንም ሰው የሸንጎ አባልም ይሁን ወይም ሚኒስትር የሕሊና ነጻነት እንዳለውና ይህን ነጻነቱን ተጠቅሞ መደገፍ መቃወም እንደሚችል የሕጉ እሴት ያረጋግጥለታል። … ማታለልና ማጫበርበር ሥልጣንን መከታ አደርጎ አገርንና ሕዝብን አደጋ ላይማንም ፖለቲከኛ መጣል እንደማይቻል ሕጉ ያግዳል ። ለዚህም ነው የመሓላ ቃል በአደባባይ የሚሰጠውም! ከሁሉም በላይ የግል ሐብትን ያረጋግጣል። የጀርመን ኢኮኖሚም ያደገው በግለሰቦች ድካምና በተመራመሪ ጠበብቶች ጥረት በሠራተኛው ሙሉ ተሳትፎና በእሱ አገርና ሥራ ወዳድነት በሦስቱ ሕብረት ነው። የአይዲኦሎጂ ዕብደት -በታሪክ እንደምናውቀው- ከዚህ በፊት በተለያዩ ዘመናት ይህችን አገር (ድፍን አውሮፓንም ጭምር) ጦርነት ውስጥ ከቶ አመድ አልብሶአት ለሁለት በመጨረሻም ከፍሎአት ሕዝቡን ችግር ላይ ጥሎም ሲጨፍርባት ከርሞአል። ይኸው የአይዲኦሎጂ ዕብደትም የምዕራብ ጀርመኑን ተወላጅ ኤርሽ ሆኔከርን -ዛር-ላንድ የተወለደውን- ምሥራቅ በርሊን ገብቶ „ዲዲአርን“ ከሠላሳ አመት በላይ እንዲገዛ አድርጎታአል። 27