ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 24

… መንገድ ጠርገዋል። ድልድይ ዘርግተዋል። ሓውልትና ሓዲዲ ሆቴልና ምግብ ቤት የመኪና ፋብሪካ ሳይቀር ተክለው ሊሞዚን ተሽከርካሪ መኪናዎችና ካሚዮኖችም ሰርተው አውጥተዋል። ጥያቄው ግን ምን ምን ዓይነቱን ሠሩ፣ ምን ግሩም መኪና ሰሩ የሚለው ነው? የምሥራቁ መኪና እነ ትራቢና እነ ቫርተቡርግ…ከማርቼዲስ እና ከቢኤም ደብሊዩ ከፖርሸና ከአውዲ ከቮልስባገንና ከኦፔል…ጋር በምንም ዓይነት አይወዳደርም። የቤትና የመንገድ የድልድይና የሓዲዲ አሰራራቸውን ምሥራቅ ጀርመን ምናልባት ከአፍሪካውይኖቹ ሊበልጥ ይችላል- የምዕራቡን ግን በምንም ዓይነት ተወዳድሮ አይደርስበትም። የሁለቱ ጀርመኖች የምርመራና የአዳዲስ ነገሮች ፈጠራ ትምህርት ቤቶቻቸውም አንድ አይደሉም። የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አላቸው። እንዴት ነው ? በምን ብልሃት ነው? ምዕራቡ ምሥራቁን ሊበልጠው የቻለው? „የቦኑ ሪፓብሊክ“ የወሰደውና የተጓዘበት መንገድ እላይ እንዳየነው ደረቅ አይዶሎጂ ሳይሆን -ትሩፋቱንም ለጊዜው እንተው- በቫሊዩ/በእሴት ላይ በተመሰረተ መፍትሔ ነው። በምሥራቅ ጀርመን ጋዜጣዎች እየታተሙ ይወጡ ነበር። ግን ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበር? ስንት ጋዜጣዎች?…. የተለያዩ አስተሳሰቦችና አመለካከቶችን ይኸው ጋዜጣቸው ያስተናግድ ነበርወይ? ሰዎች እንዲከራከሩበት ይጋብዝ ነበር? እንደ ምዕራብ ጀርመን የኮሚስቶቹም ሥርዓት እንደ አቂሚት አልፎ አልፎ ምርጫ አካሂደው በ95% ከመቶ እነሱ እራሳቸው አሸንፈው ሸንጎአቸው ውስጥ የህዝብ እንደራሴዎችን ያስቀምጡ ነበር። ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች መናገርና መጠየቅ ይፈቀድላቸዋል? 24