ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 22

ታዲያ የነገሮች አቀማመጥ እንደዚህ ከሆነ የሰው ልጆች ሁሉ ችግር ከየት መጣ? ለጀርመኑ ፈላስፋ ለማርክሲ እና ለእሱ ተከታዮች ለኮሚኒስቶቹ መልሱ ቀላልና አጭር ነው። የሒትለር -ይታወቃል አይነሳ! በእነሱ ዕምነት „በዝባዡ ክፍል-አደሃሪ“ የሚሉት መደብ ስለ አለ „ይህን ሁሉ መዓት በሰው ልጆች ላይ ያመጣውና ያወረደው እሱ ወይም እነሱ ስለሆኑ „እነሱን ደምስሰን የላብ አደሩን አምባገነን ሥርዓት ከዘረጋን ይህች ዓለም በአንዴ ወደ ገነት ትቀየራለች“ ባይ ናቸው። ኢትዮጵያም -የሚያሳዝነው ታሪካችን ይህ ነው-የመረጠቺው መንገድ ይህኛውን ነው። ሓይማኖተኛውና የሃይማኖት አስተማሪው ከዚህ ለየት ያለ አመለካከት አለው። „ሰይጣንና መጥፎ መናፍስት በዓለም ላይ ስለተበተኑ እነሱ ናቸው የችግሮቻችን ሁሉ መነሻ „ ብለው ያስተምራሉ። ለአክራሪ ፋናቲከሮች ደግሞ ሌላው ሕዝብ ተቀብሎ የሚከተለው ከእነሱ የተለየ „ እምነትና ሃይማኖት ያለው ሰው ለዓለም ሁሉ ችግር ተጠያቂ እሱ“ ነው ባይ ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ አደገኛ አመለካከትዘንድሮአፍሪካ ገብቶአል። ለመለዮ ለባሹ ለጠበንጃ ያዢው ወታደር ሳይጠየቅ እሱ እራሱ የራሱ መልስ አለው። ተማሪውም እነደ ተማሪነቱ እንደዚሁ የችኮላ መልስ ታቅፎ ቁጭ ብሎአል። „ነጻ-አውጪው“ ደግሞ በተራው ሌላ ማንም ሰው ከአለ መሪው በስተቀር የማያውቀው የራሱ „ራዕይ“ አለው። አንዴ „አዲሱ ዲሞክራቲ ነው።“ አንዴ „ብሔራዊ ዲሞክራሲ።“ አንዴ „ዲሞክራቲክ አብዮት።“ ሌላ ጊዜ ….ሶሻሊዝም ኮመኒዝምነው። ወይም መገንጠል ተብሎ ፕሮግራማቸው ላይ ተጽፎአል። የሰው ልጆች ባህሪና አካሄዳቸውን እናውቃለን የሚሉት እነሱ እንደሚሉት ከሆነ (ይህ የታሪክና የፍልስፍና የሳይኮሎጂና የሕግ ሰዎች ምራቃቸውን የዋጡትን ፖለቲከኞች ያካትታል…) ተቆጣጣሪና ተቆጪ ከልካይ ኃይልና ተቋሞች ሕግና ሥርዓት ከሌሉ ነገ „…አንተም እኔም እሱዋም እሱም ማንም አረመኔ“ ከመሆን አትመለሱም ይላሉ። 22