ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 21

እንደማመጥ ከተባለ! ምዕራብ ጀርመን አሸናፊ ሁና ሊትወጣ የቻለቺው በሚቀጥሉት አብይ ምክንያቶች ነው። መንገዳቸውን የቀየሱት ድርቅ በአለ የአምባገነን አይዲዎሎጂ አይደለም። በእሱ ሳይሆን በቫሊውስ- በእሴት ላይ በአተኮረና በእሱም ላይ በተመሰረተ አመለካከትና አሠራር ነው። እሴት ምንድነው? ምንድናቸው እነዚህ እሴቶች? የትኛው እሴት ነው ከሁሉም ወሳኝ? አንደኛው እሴት -ይህንንም ሕገ-መንግሥታቸው ላይ ገና -ሀ- ብለው ሲጀምሩ ጥሩ አድርገው አስቀምጠውታል- ይህ ደግሞ የሰው ልጆች በአጠቃላይ ከሕይወት ልምምዳቸውና ተመክሮአቸው ከሁሉም በላይ ከአምላካቸው በተፈጥሮ በእሱ አምሳል በመፈጠራቸው ያገኙት ትምህርት ነው- „የማንም ሰው ሰበአዊ መብቱና ክብሩ በማንም አይረገጥም አይደፈርም „የሚለው አንቀጻቸው ነው። ይህም አብሮ ተከባብሮ ተቻችሎና ተደጋግፎ ለመኖር የሰው ልጆች ጀርመኖች ያገኙት ጥበብና ጸጋ ከቀመሱት ከፋሺዚም እና ከኮሚኒዝም ከሁለቱ አደገኛ ፍልስፍና እና ሥርዓት ከእነሱ - እመኑኝ! ያገኙት ዕውቀት ነው ። እርግጥ በዚህች አጭር ጽሑፍ ከድንጋይ ዳቦ ዘመን ተነስተን ወደ 1948ቱ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ መግለጫ ድረስ አሁን መጥተን ሁሉን ነገር ገበታው ላይ ዘርግተን ማሳየት አንችልም። በአጠቃላይ የሰው ልጆች ከጠብ ይልቅ ፍቅርን እንደሚመርጡ ማንኛችንም በደንብ እናውቃለን። በጦርነት ፋንታ ሰላምን ከመበታተን አንድነትን፣ ከሥራዓተ አልባነት ይልቅ መልካም አስተዳደርን፣ ከቀማኛነት መልካም ሥነ ምግባርን ከተንኮል መረዳዳትን ከበደል ፍርድን….እነዚህን ሁሉ የሰው ልጆች እንደሚያስቀድሙና እንደሚመርጡ ይህን ስለምናውቅ ይህን ስለምንረዳ መድገሙ አስፈላጊ አይደለም። 21