ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 20

ሁነው- በዓለም ፖለቲካ ምድር ላይ ብቅ ያሉት? እንግዲህ በመጨረሻውም :ለምንድነው የምዕራብ ጀርመን የዛሬ ሃያ አምስት አመት አሸናፊ ሁኖ የወጣው? ለምንድነውስ የምሥራቅ ጀርመኑ የኮሚኒስቶች ሥርዓት ተንኮታኩቶ የወደቀው? በሌላ አነጋገር ለምንድነው የኮሚኒስቶቹ ሥርዓት ብቻዬን ልግዛ ብሎ አጥር አጥሮ በጠበንጃ አፈ ሙዝ ሲገዛ ከርሞ በሁዋላ ሳይታሰብ በሰላማዊ የሕዝብ አመጽ ሊወድቅ የቻለው? እንዴትስ ወደቁ ? ለምንድነው ምዕራብ ጀርመን በሸንጎ ምርጫ ከፖለቲከኞቹ ለመገላገል ይህኛውን ሰላማዊ መንገድ እንደ መፍትሔ የመረጠው? የተለያዩ የፖለቲከ ድርጅት መሪዎችና አባሎቻቸው በነጻ-የፓርላማ ምርጫ ውድድር ውስጥ ገብተው ለመሳተፍ ለምን ተስማሙ? የጀርመን ኢኮኖሚንስ (የምዕራቡ) እንዴትና በምን ብልሃት ነው ከወደቀበትና አመድ ከለበሰበት ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በሁዋላ ( ኢትዮጵያ የዛሬን አያድርገውና ስንዴና የብርድ ልብስ እንዲሁም ቡና ለጀርመን፣ ለእንግሊዚ ለጃፓን በጊዜው ዕርዳታ ሰጥታለች) አሥራ ሁለት አመት በአልሞላ አጭር ጊዜ ውስጥ በልዩ ተአምር ከመቀመቅ ተነስቶ በአንዴ -በስድሳው አመተ ምህረት – ዓለምን ሊያስገርም የቻለው?… እረ ብልሃቱ፣ የእነሱ ብልሃታቸው ምንድነው? ምን ነበር? በመጨረሻው እንደገና በምን ብልሃትና ዘዴ ነው? በየትኛው መንገድ ነው? የጀርመኑ የፖለቲካና የኢኮነሚ ሥርዓት አሁን ሌሎቹ አገሮችና መንግሥታት በኢኮኖሚና በፊናንስ ቀውስ ውስጥ ገብተው ሲማቅቁ እነሱ በአውሮፓ/በዓለምም ውስጥ ጠንካራ ሁነው ሊወጡ የቻሉት? መ መልሱ አጭር ነው። 20