ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 18

ይከታል። ቢቀር ቢቀር እነሱን አጠፋችሁ ብሎ እሥር ቤት ያስወረውራል። ትልቁንም ትንሹንም አመሰቃቅሎ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ ያጨራርሳል። ምንም የማያውቀውንም እሳት ውስጥ ከቶ ያስጨርሳል። የዞረበት አይዲኦሎጂ ደግሞ አንድን ሰው እላይ ሰቅሎ መላ ሕብረተሰቡን ወደ የግል ሐብት ወደ እሥር ቤትም እንዳለ ይቀይራል። ሱማሌና…ሩዋንዳ ብሩንዲና ኬንያ፣ ሱዳናና ደቡብ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የመን፣ ኮንጎ እና መካከለኛው አፍሪካ፣ ግብጽ ሊቢያ ማሊና ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ ኡጋንዳ ኢትዮጵያና ኤርትራ …ኢራክ፣ ሶሪያ ሊባኖስ አፍጋኒስታን … እነዚህ ሁሉ አገሮች የሚተረማመሱት እርስ በራሳቸው የሚፋጁት በሌላ ነገር ሳይሆን ከውስጥ ሆነ ከውጭ በተወረወረላቸው በማያስማማ አደገኛ አይዶሎጂ ነው። ያንን ያዝን ብለው በሚያምኑት ርዕዮተ ዓለምም በእሱ ሳቢያ በተቆሰቆሰው እሳት አንዱ ተነስቶ በሌላው ላይ ጦር አውጆል። ያኛው በዚህኛው ይህኛው በዚያኛው ላይ ተነስቶአል። ሁሉም በአንዱ ላይ። አንዱ ብቻው