ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 16

ሌላው ተነስቶ „…አወቂ ሲጫወት ልጆች እየተነሱ ጣልቃ እንዳይገቡ ቁጥጥር ይደረግ „ ብሎ ማሳሰቢያውን ለቤቱ ያቀርባል። እሱም ሓሳብ ማሰሪያ ሳያገኝ እንደገና አንድ ያልታሰበ ነገር ስብሰባውን እንዳለ ገልብጦ በሰከንድ ውስጥ በጭንቅላቱ ያቆመዋል። አንድ ተንኮለኛ ዘበኛ- እነሱ ሲቦጫጨቁ ቁጭ ብሎ ማየቱን ይወዳል- የውሾቹን ስም አንድ በአንድ „ አንተ …ውስኪ…ቦቢ ዘብ ይደሩ የት ነህ?…እነ ነብሮ እነ ግሥላ እነ ፑሺኪን እነ ሉሉ … የትናችሁ…ተመልከቱ…“እያለ እየተጣራ እንደተለመደው እነሱ ሲቦጫጨቁ ቁጭ ብሎ እግሩን ዘርግቶ ለመሳቅ አንድ አጥንት እያሽከረከረ ያ ተንኮለኛ ዘበኛ መሓላቸው ይጥላል። ግልጽ ነው። ያችን አጥንት ለብቻው ቀምቶ ለመብላት ወንዱም ሴቱም ብድግ ብለው ተያያዙ። በቅጽበት በትንሽ ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ያ በሰላም የተጠራው ስብሰባ ወደ ጦር ሜዳ ተቀየረ። ሁሉም አፈር ለበሱ። እንደፈለገው ተቦጫጨቁለት። ምን መጣ ብለው ቡችሎቹም ሸሽተው አፋፍ ላይ ቆመው ይህን ጉድ – እነሱም ነፍስ ሲገዙ የሚገቡበትን ነገር- ትንሽ ኮረብታ ላይ ሁነው መመልከት ጀመሩ። ሁለተኛው አጥንት በሌላ ዘበኛ ተወርውሮ እፎይ ሳይሉ መሓላቸው ወደቀ። እንደገና የይገባኛል/አይገባህም ግብግቡ በመካከላቸው ተከፈተ። አጥንቱዋም አፈር ትለብሳለች። በጥቂት ደቂቃ ከፊሉ ውሻ ቆስሎ በዚያች ትንሽ ጊዜ ውስጥ ያነክሳል። ሌላው ቁስሉን መላስ ጀምሮአል። አፍንጫው የደማ አለ… ቆዳው የተቀደደ። ጭንቅላቱንና ጆሮውን የሚነቀንቅ አለ። ቁና ቁናቸውን ይተነፍሳሉ። ያ ፈረንጆች ቤት „ለጥቂት ጊዜያት በልጅነቴ አሳልፌ ነበር“ ያለው ውሻ ቡችሎቹን ሰብስቦ „ ከዚህ የውሻ መብት ከማይከበርበት አገር ጠፍቶ 16