ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 15

ሲመጣ -ብዙም ሊሆኑ ይችላሉ – ወጣ ብለን ከጌቶቻችን ጋር ሁነን ሳንጮህና ሳናስፈራራቸው እግራቸ ሥር እየተሽከረከርን በደስታ እንቀበላቸዋለን። „ከሌላም ከማናቀው ውሻም ጋር እንደዚሁ ገበያ ላይ ወይም ንፋስ ለመቀበል ለሽርሽር ስንወጣ ሜዳ ላይ ከተገናኘን ተጠያይቀን ትንሽ ‚እመቤትሽ የለበሸቺው ቀሚስ ጌታህ የያዘው ከዘራ ወይም ክራቫት ብለን ተቀላልደን‘ መንገዳችንን እንቀጥላለን እንጅ እዚህ እንደማየው አንዱን ሰብሰብን ብለን አሳደን አንቦጫጭቀውም። እናንተ እኔ ይህ ሳጫውታችሁ ‚አውሬነትህን ረሳኸው ብላችሁ እንደምትስቁብኝ አውቃለሁ። „ምግባችንን ከሳህናችን ላይ እንበላለን እንጅ ጌቶች ሲበሉ ሆነ ልጆች ዳቦአቸውን አስቀምጠው ሲጫወቱ ቦጭቀን እናንተ እንደምታደርጉት አንሮጥም። በዚያም ሳቢያ ጥዋት ማታ በድንጋይ አንደበደብም። አሁን ያቺ ድመት በዚህ ስታልፍ የሆነውን አይቼአለሁ። ከቤት ድመቶችም ጋር አብረን እንውላለን እንጅ አንጣላም። ምንም የሚያጣላን ምክንያት የለም። እሱዋ እራሱዋ አይጥ አይታ ስትፈራና እኔ ጋ መጥታ ስትወሸቅ አብረን እንስቃለን እንጅ እሱዋን አሳደን ጊዜአችንን በዚህ አናጠፋም…በጊዜአችን ሌላ ስንት የሚሰራ ነገር አለ። እኔ ለምሳሌ አስተማሪ ተቀጥሮልኝ ጋዜጣ ጥዋት ጥዋት ለጌታዬ ለማምጣት ትምህርት ወስጄ ነበር። ሌሎቹ ሲማሩም አ…“ እያለ እላይ የተሰነዘሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሙከራ በሚያደርግበት ደቂቃ አንዱ ዕድሜው ጠና ያለ ውሻ ተነስቶ „…ምን ይደረግ አንተ ‚ችሎ ማደር‘፣ አንተ እኮ ነህ በዚህ ውርጋጥ ዛሬ የምታሰድበን። እንተ እንደዚህ እኛ እንደዚያ እያለ …ይህ ትላንት የመጣ ጥጋበኛ ውሻ እኛን እየሰደበን ነው። የልብህን እየተናገርክ የስድብ ናዳ አወረድክብን …። እግዚሔር ይስጥህ። ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተ ስብሰባውን የጠራኸው አቶ ‚ችሎ ማደር ነህ!“ ብሎ ጋባዡንም ተናጋሪውንም በወቀሳ ያዋክባል። 15