ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 8

ሁለት ወገኖች እናያለን። ለአንደኛው „ኢትዮጵያ“ የግል ሐብቱ ናት። እንደምናየው እሱም እንደፈለገው በቃላትም በገንዘብም እንደ ግል ንብረቱ „…ይሸጣታል። ይለውጣታል።“ ለሁለተኛው -እሱ ስለ ከዳት- ብትኖር ብትጠፋም እንደምናነበው ቅንጣት ያህል እንኳን ግድ የለውም። እንደ ምንም ብሎ በዚያም በዚህም አድረጎ ድል አድረጎ ቤተ-መንግሥት ለገባው ሰው ሁሉ ይህች አገር እዚያም ምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ „የግል“ ሐብቱ ነውና ቢፈልግ ከመሬቱ ሊነቅለው ይችላል። ሊያባረውም።ሊያስረውም ። ሊቀጣውና ተደጋግሞ በተለያዩ ዘመናት እንደታየው ሊገድለውም ይችላል። ደርግ እንደዚህ አድርጎ ነው በግዛት ዘመኑ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ያኔ ያየው። እህአዴግ ሻብዕያና ለጥቂት ጊዜያቶች አብሮ ከሁለቱ ጋር ለሠራው ኦነግ – ድል አድራጊ እነሱ በዘመናቸው ስለነበሩ- „ሁሉም ነገር“ ጊዜውም ዘመኑም ንብረቱም የኛ ነው ብለው የመጀመሪያው አመታት ላይ እነሱ እራሳቸው እንደጻፉት እስከመተናነቅ ድረስ ሄደዋል። ። ድሮ 8