ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 4

አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial) Published February 28, 2014 አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial)| አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial) እንደ ጀመርነው በየወሩ አንዳንድ ጉዳዮችን- ውድ አንባቢ- እናነሳለን። ዛሬም እንደገና ኢትዮጵያ የማን ናት? ብለን እናንተንም እንጠይቃልን። ዩናይትድ እስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሆነች ወይም ፈረንሣይ ወይም ደግሞ ደቡብ አፍሪካ የአሸናፊው ፓርቲ „ የግል ንብረትና የግል ሐብት“ እንዳልሆነች ሁላችንም እናውቃለን። በተቃራኒው ቻይና ወይም ሰሜን ኮሪያ ወይም ደግሞ ኪዩባ የአሸናፊው ድርጅት ያውም የመሪው ቁንጮ „የግል ንብረት“- እነሱ በቃላት ጨዋታ „የጭቁኑ ሕዝብ“ ጥዋት ማታ ይበሉ እንጂ-መሆናቸውን በደንብ ይህንንም ጉዳይ ለይተን እናውቃለን። እንረዳለን። ….ኢትዮጵያ የማን ናት? ኤርትራስ ? ኦሮሞና… አማራስ? የሚለውንም ጥያቄ የምንሰነዝረው -ዘለቅ ብላችሁ አንደምትመለከቱት- ከዚሁ አንጻር ነው። አንዳንዴ ይህ የስታሊን ቲዎሪና ትምህርት ኢትዮጵያ ባይገባና ባይስፋፋ ኑሮ ሰው ሳያልቅ ትውልዱ በነገር ሳይሳከር ይህች አገር በሥልጣኔዋ እንደ ሌሎቹ መንግሥታትና ሕዝብ የትና የት በደረሰች ነበር እንላለን። … ደርግም ነጻ-አውጪም ጦርነትም ስደትም ክትትልም አምባገነነንትም አለመደማመጥና አለመግባባትም የሚባለውም ነገር በልጆቹዋ መካከል ፈጽሞ በአልተፈጠረም ነበር ብለን እንገምታለን። 4