ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 38

አይሁዱም ክርስቲያኑም እስላሙም የሚያምነውና የሚጸልየው -ይህ ደግሞ አቴኢስቱን አይጨምርም- ለአንድ ፈጣሪው አምላኩ ለእግዚአብሔር ነው። ይህ ነው እንግዲህ ዋናው ነጥብ እነሱን አማኞቹን በኢትዮጵያ አንድ የሚያደርጋቸው መንፈስ ነው። አንድ ቦታ ላይ ስለ ኢትዮጵያኖች የምግብ አሰራር፣ስለ የጋራ ሸማ ልብሳቸው፣ ስለጥልፍ ቀሚሳቸውና ቡሉኮአቸው የቤት ቁሳቁሳቸውና የጋራ በዓላቸው ሠርግና ሐዘናቸው ቀብራቸውና ለቅሶአቸው ጭፈራና ድግሳቸው ደቦና አፈርሳታ አንስተን አልፈን ነበር። ከዚሁ ጋር ስለልማድና ስለባህላችን ስለተትሩፋትና ስለትውፈታችን ስለሥነ ምግባራችንና ስለእሴታችን ስለ ግብረ ገብ ትምህርትና ስለ አስተዳደጋችን ስለ እነዚህ ሁሉ እኛን ከጎረቤትም አገር ከሌላው ዓለም ልዩ ከሚያደርጉን ነገሮች ከብዙ በጥቂቱ በአለፈው ጊዜ እንደዚሁ አንስተን አልፈናል። ድርሰቶቻችንና ጽሑፎቻችን አሉ። ታሪክና ምሴሌዎቻችን አሉ። ተረትና ጨዋታዎች። ዘፈንና ጭፈራዎች። የሙዚቃ መሣሪያዎቻችን ዋሽንትና መለከት ከበሮና ድቤ ጦርና ጋሻ ቀረርቶና እንጉርጉሮ… በዚያ ላይ አንድ የሚያደርገን የስፖትር ጨዋታም አለ። ማን ነው ለመሆኑ የአገሩ ልጅ ማራቶን ሮጦ ሲያሸንፍ ሳይዘል ቁጭ ብሎ የሚያየው?… አሥር እና አምስት ሺህ ስምንት መቶና ሦስት ሺህ…ተከታትለው ሲገቡ የ ማይፈነድቀው? ኳስ ሲጫወቱ አብሮ የማይጨነቀው? ፭ ግን ደግሞ የአበሻ ልብስ የማይለብሰውን ቴሌቭዢን የሌለውን ባዶ እግሩን የሚሄደውንና መጻፍ ማንበብ የማይችለውን የገጠር ሰው እሱን „ኢትዮጵያዊ አይደለም“ ልንል እንችላለን? የደቡቡ የዶሮ ወጥ አሰራር ከሰሜኑ ይለያል? የሸክላ ድስት ምጣድና አኩንባሎ ቡናውና ዕጣኑ ጠላና ጠጁ እንጀራና ዳቦው እነዚህ ሁሉ ምንድናቸው? 38