ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 37

መልሳችን አጭር ነው። የትም ቦታ የለም።ሁሉም በኃይል ነው የተዋቀረው። የኢትዮጵያ ታሪክ አነሳስና አካሄድ ከአሜሪካኑና ከእንግሊዙ ከጀርመኑና ከሩሲያው ከፈረንሣዩና ከጃፓኑ ከኬንያኑና ከደቡብ አፍሪካው አመሰራረትና አመጣጥ ፈጽሞ የተለየ አይደለም። ፫ ለጋና እና ለናይጄሪያ ለሕንድና ለታላቁዋ ብርታኒያ ለአሜሪካና ለአውስትራሊያ የጋራ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ ነው። ይህ ስለተባለ ግን ሌላ ቋንቋ የእነዚህ አገር ኑዋሪዎች አይናገሩም ማለት አይደለም። በዘልማድ እንግሊዝ በሚባለውም ታላቁዋ ብርታኒያ እዚያ አገር አየር ላንድ ዌልስ ስኮትላንድ የሚባሉ አካባቢና የተለያዩ ቋንቋዎች እናያለን፣ እንሰማለን። ግን ሁሉም የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ነው። እሱም ከሌላ ቦታ የመጣው እንግሊዘኛ ነው።የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዕድሜው ደግሞ ረጅም አይደለም። በሩሲያና በኬንያ በሕንድና በኮንጎ በደቡብ አፍሪካም ብዙ የተለያዩ ቋንቋ የሚናገሩ ዘሮች አሉ። ግን አንድ የመማሪያና የመግባቢያ የገበያ ላይ መለዋወጫና መነጋገሪያ ቋንቋ ከመጠቀም እነሱን የሚያግዳቸው ነገር የለም። አማርኛ ከግዕዝ በሁዋላ ለኢትዮጵያ እንደሆነው ሁሉ ለቻድና ለሴንጋል ለአይቮሪ ኮስትና ለኮንጎ ለእነሱ ደግሞ የአውሮፓው ፈረንሣይኛ ስፓንሽና ፖርቱጋል… እንደ አካባቢው የጋራ ቋንቋቸው ሁኖ እነሱን ከጥቂት አመታት ወዲህ ያገለግሉአቸዋል። ፬ ቀደም ሲል ሃይማኖትን አንስተን በኢትዮጵያ ሦስት ትላልቅ ሃይማኖቶች እንዳሉ ጠቀስን እንጂ አንድ የሚያደርጋቸውን ስለ አንድ „አሃዱ አምላካቸው“ ሳናነሳ አልፈናል። 37