ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 29

እንደፈለጉት የሚያወርዱት በደል ከዚያም በላይ ደስ እንዳላቸው የሚጠቀሙት ኃይልና ጉልበት በመጨረሻም የሚያሳዩት „ጭካኔ ዝም ተብሎ አይታለፍም „ ባይ ናቸው። ጸሓፊዎቹ እንደሚሉት (በመጀመሪያ ረጋ ብለን እናዳምጣቸው) የሰው ልጆች የበላይነት ቦታ በዚህቺ ዓለም ላይ መያዝና መወሰን- ይህ ቀጥለን የምናነሳው ጉዳይ – አጠያያቂ ነው ባይ ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ደግሞ በእንስሳ ላይ ብቻ ሳይሆን „ ሕግና ሥርዓት በሌለበት አካባቢም“ በሰው ልጆችም ላይ ሌሎች ሰዎች የሚደርጉት በደል እንደዚሁ ጎልቶ የሚታይ ጉዳይ ነው። አንድ ሰው ሓብቱን ወይም ጠበንጃውን መከታ አድርጎ ወይም ወታደር አሰልፎ ወይም ደግሞ አስፈራሪና አጃቢ ደጋፊ ጋሻ ጃግሬዎቹን አሰልፎ በገዛ ወንድሙ ላይ ከሚያሳየው ባህሪ ጋርእኩል በእንስሳት ላይ የሚወርደው ፍጅት -በእነሱ ዓይን – እነሱ እነደሚሉት አንድ ነው ባይ ናቸው። እሱም ሌላ ነገር ሳይሆን ኃይልና ጉልበት ነው። ጸሓፊዎቹ ኃይልና ጉልበትን „በደካማ ፍጡሮች ላይ መጠቀም ይቁም“ ባይናቸው። ሥልጣኑንም መከታ አድርጎ አንዱ በአንደኛው ላይ ኃይልና ጉልበቱን መከታ በማድረግ ያ ሰው የሚወስደው ኢሰበአዊ እርምጃ ደግሞ „ማን ፈቀደለት?“ የሚለውን ትልቁን የህግ -የሌጋሲ ጥያቄ ያስነሳል። ይህን ጥያቄ ማንሳት ደግሞ በቀጥታ የፖለቲካ ፈላስፋዎች እንደሚሉት የዚህችዓለምን ችግር በትክክል ለመረዳት- ይጠቅማል። በሌላ አነጋገር ብዙዎቹ እዚህ ተስማምተው እንደሚሉት በእንስሰና በከብቶች ላይ የሚወርደው የሚዘንበው ኃይልና ጉልበት ዱላና ድብደባ እሥራትና ሰንሰለት ሸክምና ጭካኔና ቆይቶም በአንዳንዱ ላይ በመጨረሻ የሚደርሰው የቢላ እርድ…ይህን ሁሉ -ጸሓፊዎቹ እነሱ እንደሚሉት እያዩ ሳይናገሩ ዝም ብሎ ዘሎ ማለፍ በሞራል ደረጃ እንደማይቻል በጻፉት ጽሑፎቻቸው ላይ እነሱ አንስተዋል። 29