ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 25

እሱም ማንም ሰው እንደሚያውቀው በከብቶች ላይ የሚደረገውን በደልና ጭካኔ ነው። ነገሩ ከኢትዮጵያ ለመጣ ሰው አዲስ አይደለም። ከብቶች በፍልጥና በጅራፍ፣ በድንጋይና በዱላ በጅራፍና በአለንጋ ይገረፋሉ። ይደበደባሉ። አለፍላጎታቸው ከብት በመሆናቸው ይታሰራሉ እንዲያርሱም ይደረጋሉ ከአቅማቸው በላይ ይሸከማሉ ይህን ሁሉ ፍዳ ከአዩ በሁዋላ ደግሞ አንድ ቀን እንደ አሮጌ ጫማ አንዳንዶቹ (ቆዳው የእነሱ ነው) ከቤታቸው ተባረው ሜዳ ላይ ይጣላሉ። የተቀሩት ደልበው ቋቅ እስከሚላቸው ድረስ በግድ ተቀልበው በሁዋላ ተሸጠው እንዲታረዱ ይደረጋሉ። ይሀ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?የሚለው ጥያቄ ጸሓፊዎቹን አንገብግቦአል። በመጀመሪያ ግልጽ እንዲሆን „ይህን ለማድረግ ተንቀሳቃሽ ነፍስ በአለው በአንድ ከብት ላይ ለእኛ ለሰው ልጆች ማን ፈቀደልን?“ የሚሉ ሰዎች እዚህ ተነስተዋል። D ሁለቱም ሦስቱም ጸሓፊዎች በዓለም ላይ 56 ቢሊዮን ከብቶች በዓለም ላይ ታርደው – ይህ ቁጥር ከባህርና ከውቅያኖስ ከጫካና ከወንዝ ተለቅመው የሚወጡትን ትናንሽ ነፍሳትናንና ዓሣን ሌሎቹ ሕዝቦች እያጣፈጡ የሚበሉትን ቅንቡርስንና እንቁራሪቶችን ትሎችንና ጉንዳኖችን አያካትትም- ለምግብ ይቀርባሉ ብለው ይከሳሉ። ለሒላል ሴስጊን ይህ ድርጊት ደር ሽፒግል ለሚባለው የጀርመን መጽሔት ተጠይቃ ስትመልስ እንዳለቺው „…በእንስሳትና በከብት ላይ የታወጀ ርህራሄ የሌለው ፍጅት ነው“ ብላላች። ዶሮና አሣማ ላምና በግ ጥንቸልና ዳኪዬ በሰው ሰራሽ ዘዴ እንዲራቡ ቶሎ እንዲደልቡ ተደርገው ታርደው ለገበያ ይቀርባሉ…ይህን ለማድረግ የሰው ልጅ የሞራል መብቱን ማን ሰጠው ይላሉ? ሦስቱም ጸሓፊዎች የሚጠቀሙበት መንገድና የሚከተሉት ጎዳና የሞራል ፍልስፍና ነው። 25