ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 20

ሁለት አማራጭ መፍትሔዎች መገመት ይቻላል። የትኛው ትክክለኛ እንደሆነ -የመጀመሪያው ይሁን ሁለተኛው- መልሱን ለማወቅ በጣም ያስቸጋራል። እንደዚሁ ለማወቅ የሚያስቸግረው ነገር የሮማው ሊቃነ ጳጳስ ክሌመንስ ሰባተኛው ለኣይርላንዱ ተቃዋሚዎች ከቤተ- ክርስቲያኑዋ ተገንጥለው „በአፈነገጡት“ በእንግሊዞች ላይ እንዲነሱ ለማበረታቻ ላኩ የተባለው ባለወርቅማው የፎንቅስ ላባ ዕውነተኛ ታሪክ ይሁን አይሁን ነው፤ስለ እሱም ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ግን ቢያንስ በየአምስት መቶ አመቱ በተከታታይ አደጋና መከራ ላይ ይህች አገር ወድቃ ትንሣኤዋን ሁሌ – በታሪኩዋ ላይ እንደታየው ከአመድ ወጥታ ብቅ ብላ እንደገና ታድሳ እንደተቋቋመች እናውቃለን። ከአምስት መቶ አመት በፊት የተካሄደው የግራኝ መሓመድ ወረራ አንደኛው ነው። ከዚያ በፊት ከአምስት መቶ አመት በፊት የተካሄደው የዮዲት ጉዲት ሥራና ጥፋት ሁለተኛው ነው። የኢትዮጵያ ግዛት የተስፋፋበት የአጼ ካሌብ ዘመን ሦስተኛው ነው። አሁን ያለንበት አንዱ አንደኛውን የማይሰማበትና ሌላውን ጨርሶ የማያደምጥበት ዘመን ሌላው የፈተና ጊዜ ነው። ይህ ከሆነ ቢያንስ አርባ ሃምሣ ዓመት አይሆነውም? ዓለም እንዴት እንደተፈጠረችና ጠፈር -ዩኒቨርስ እንዴት መስመሩዋን ይዛ ሳትጋጭ እንደምትንቀሳቀስ የሕይወት እስትንፋስ- ነፍሳችን ምን እንደሆነች? ብዙዎቹ ነገሮች ከዕውቀታችን በላይና ውጭ ስለሆኑ ይህ ነው ይህ ነው ብለን አሁን መናገር አንችልም። የሚደጋገመው የሰው ልጅ ሆነ የእህል ዘር… መሬት ላይ ይወድቃል። ይበሰብሳል።እንደገናም ይበቅላል። ተመልሶም ይነሳል።ይህ ደግሞ አዲስ አይደለም። ዱሮም እንደዚህ ነበር። አሁንም ወደፊትም እንደዚሁ ይቀጥላል። „የትንሣኤ“ ምልክት የሆነውን ፎንቅስን ታሪክ ዛሬ ያነሳነው ኢትዮጵያን ዘለዓላማዊ ከሚያደርጉአት ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን ንግርት፣ 20