ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 19

የአገሪቱን አዕዋፋትን አስከትሎና በእነሱ ታጅቦ ወደ ግብጽ አገር „ ደራሲው ላክታንዝ ቀጥሎ እንደጻፈው“ …ዘልቆ ሒሊዮፖሊስ የሚባለው ከተማ ይገባል። አመጣጡ ከዚህቺ ዓለም ተሰናብቶ ለማለፍ ነው።“ የአሟሟቱ ሥነ-ሥርዓት ግን ልዩ ነው። „…መልካም ሽታ ያለው እጣን እና ከርቤ ተነስንሶለት የወይራ እንጨት እና ጥሩ ማአዛ ያላቸው ቅጠሎች ተጎዝጉዞለት „ እዚያ የአደባባይ አልጋ ላይ ተጋድሞ በቀጠሎው የግብጽ ጸሓይ ጨረር በእሱ ተለኩሶ ነዶ ጋይቶ መልካሙ ጢስ ወደ ላይ እየተና አመዱ እዚያው ጠረኑን እየለቀቀ ነፍሱ ወደ ላይ እንድታርግ ፈልጎ ነው ይባላል። ከተቃጠለው ላባው፣ሥጋውና አጥንቱ ከወደቀው አመዱ ውስጥ ግን የታሪኩ ተአምር ይህ ነው- ነፍሱ ሳትሆን ወደ ላይ የወጣችው „…አዲስ እሱን የመሰለ አሞራ… „ ወይም ደግሞ እንደ ገና የዱሮው ታድሶና ተመልሶ ወጣት ሁኖ በእሳት ተፈትኖ „ተወልዶ“ ከዚያ አመድ ተራግፎ ብቅ ብሎ ወጥቶአል። „…እንዴት ያለህ የተባረክ አሞራ ነህ። ሞትን አትፈራም። አንተው እራስህ የእራስህ ፈጣሪ b