ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 18

ደኑን ከአልበላው የውሃ ጥፋትግሩም መናፈሻ ገነቱን ከአልመታውና ከአላጠፋው ከኢትዮጵያ ምድር ነው። የትውልድ አገሩም ደስ የሚለው የኢትዮጵያ መዝናኛ ሜዳና ሸለቆ ተራራና ዱር ነው።“ ስለዚህ አሞራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው በጥንታዊ የግሪኮች የአተራረክ ዘመን ነው። እኔ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁትና ያወኩት ግሪክ አገርን ስጎበኝ ሳይሆን ጥንታዊዋን የንግድ ከተማ ባህር ላይ ደስ በሚል አርችቴክቶች የተሰራቺውን ቬኒስያን ለሁለተኛ ጊዜ ወርጄ እዚያ በሰነበትኩበት ቀናት ነው። በመጀመሪያው ጉብኝቴ የማርቆስ ቤተክርስቲያን እና ከተማይቱ የያዘቺውን ደስ የሚሉ የባህር ዳር መናፈሻ ቦታዎችን- የጀልባ ሽርሽሩ አይነሳ -በተለይ የቅዱስ ማርቆስ ታሪክና ከዚያም በላይ የጣሊያን ሠዓሊዎች የሠሩትን ድንቅ ሥራ እየተዘዋወርኩ(ልቤን ማርከው ነበር) እነሱን ሳደንቅና ስመለከት የቆይታ ጊዜዬን በእነሱ ላይ አጥፍቼ ሌሎቹን ቦታዎች ሳላዳርስ ተመልሼ ነበር። በሁለተኛው ጉብኝቴ በቂ ጊዜ አግኝቼ ወይዘሮ ማሪያ ካላስ በወጣትነት ዘመኑዋ ትጫወትበት የነበረውን የኦፔራ አዳራሽ – ድምጹዋ ግሩም ነው- እሱን ለመመልከት የተሰጠኝን በእጄ ላይ የሚገኘውን አጃቢ ቴፕ ገና በሩ ላይ ስከፍት በእንግሊዘኛ እና በጀርመንኛ ቋንቋ ስለ ኢትዮጵያው ወፍ ስለ ግሩሙ አሞራ ስለ ፎንቅስ – ሕንጻው አዳራሹ በእሱ ነው የተሰየመው – አንዴ በጆሮዬ ቀስ እያለ ሰውዬው ሲተርክልኝ ተገርሜ ቆሜ ስለ እሱ ከአዳመጥኩኝ ወዲህ ነው። ትዝ ይለኛል- ዞር ብዬ አጠገቤ የነበሩትን ሰዎች ሳይ -አንድ ዓይነት ነገር ነው ለካስ የምናዳምጠው- ጭንቅላታቸውን ሲነቀንቁ ስለ ምን እንደሆን ገብቶኛል። በሁዋላ እሱንንና ሌሎቹን ከኢትዮጵያ ጋር የሚገናኙ ታሪኮችንና አፈታሪኮች ንግርትና ድርሰቶችን ከግሪክና ከሮማውያን ጽሑፎች ከአረብ ጸሓፊዎች መሰብሰብ ጀመርኩኝ። አንደኛው እንግዲህ ይህ ነው። „…በተከታታይ ለአምስት መቶ አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖረ በሁዋላ ይህ አሞራ እንደ ንጉሣቸው የሚመለከቱትንና የሚያዩትን የተለያዩ 18