ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 13

ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ተደርጎ ታይቶአል። ይህ ደግሞ በሦስት ነገሮች (ሌላው ዓለም በዚህ ነው የተገራው) ከእንግዲህ በሰላም እኛም እንደሌሎቹ ሕዝቦችና መንግሥታት እንኑር ከአልን መታገድ ይገባዋል። አንደኛው በነጻ ምርጫና በሥልጣን ዘመን ላይ የጊዜ ገደብ ሲቀመጥ ነው። ሁለተኛው በሥልጣን ክፍፍልና ሽንሸና እሱን በሚቆጣጠሩ ተቋሞች „ገዢው“ መደብ እጅና እግሩ በሕግ„ተተብትቦ“ ተከቦ ሲያዝ ነው ። ከሁሉም ሦስተኛው የሰበዓዊ መብቶች ተከብሮ ሰው ሁሉ „ገዢውም ሆነ ተገዢውም“ በሕግ ፊት አለ አድሎ እኩል ሁነው ሲቆሙም ብቻ ነው። 6 ኢትዮጵያ የማን ናት? የሚለው ጥያቄ ኢትዮጵያ የእኛ ናት በሚለው በብዙ ሚሊዮን በሚቆጠሩ ዜጎቹዋ ይመለሳል። ይህ ደግሞ በምንም ዓይነት ኢትዮጵያ የጥቂት የተደራጁ ሰዎች የግል ሐብት አይደለችም የሚለውን አመለካከት ያጠናክራል። የኢትዮጵያ ችግር የመጣው ይኸው ችግር ከአርባ አመት በላይ የሰነበተብን አሁንም ከዚያ ወጥተን ወደፊት እንደሌሎቹ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መራመድ ያልቻለነው