ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 12

አንድ አገር አንድ መንግሥት አንድ መሬት አንድ ክልል የአንድ ድርጅት የአንድ ቡድን ወይም ደግሞ የአንድ የታጠቀ ወይም ያልታጠቀ ኃይል ንብረትና ሓብት አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ ሆኖአል። ለምሳሌ ኤርትራ። አንድ አገር አንድ ሕዝብ የአንድ ቡድን ሓብት ከሆነ ሁሉም እንደ ቅርጫ ለመቀራመት የሚነሳበት የሽፍቶች መፋለሚያ ሜዳና ጫካ ሆነ ማለት ነው። ይህም በአገራችን ሁኖአል። አሁን በድፍን አፍሪካ የምናየውም ሥዕል ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። በግብጽ የጦር ሠራዊቱ በአፍጋኒስታን ታሊባኑ በኢራን አያቶላዎቹ በሱማሌ እያንዳንዳኑ ጎሣ በኮንጎ የታጠቀ ሽፍታ በቻድና በሴንትራል አፍሪካ ወይም ደግሞ በናይጄሪያ የሃይማኖት ሚሊሻ አገራቸውና አካባቢው ወይም ሕዝቡ በጠቅላላው „የእኛ ነው“ ብለው እንደ ሓብታቸው የሚያዩ ክፍሎች ናቸው። ማን መርቆ ሰጣቸው? እንደዚህ ዓይነቱ ጥያቄ እንዳይነሳ እንዲያውም እንዳይታሰብ ማገድ ይችሉበታል። 5 ደርግ ለአሥራ ሰባት አመት እንደዚህ ዓይነቱን አመለካከትና የአገዛዝ ሥልት ከድሬዎቹን „የለውጥ ሐዋሪያ“ ብሎ ሰይሞ ለብቻው በአገሪቱ ላይ እግሩን ዘርግቶ ተበትኖአል። ከዚያ በፊት ንጉሠ ነገሥቱ ከመሣፍንቶቹ ጋር የበላይነቱን ይዘው ጸጥ ለጥ አድርገው ገዝተዋል። ሌሎቹ ሞክረው ሳይሳካላቸው ተቀጭተው ቀርተዋል። ከዚያ በሁዋላ ጊዜው እንደምናውቀው ለሁለት ና ሦስት ድርጅቶች አመችቶአል። በምንም ዓይነት አንድ ቡድን (የታጠቀ ይሁን ያልታጠቀ) ለአንድ አገር ውስጣዊ ችግር እሱ እራሱ ብቻውን መፍትሔ አቅራቢ መፍትሔ ፈላጊ መፍትሔ ሰጪና ለመፍትሔውም ትክክለኛ ፍርድ ሰጪ እሱ ሊሆን አይችልም። 12