ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 9

የኢህፓና የመኢሶን „ጠብ“ የምንረዳው የደርግና የሻብዕያ የጀበሃና የሻብዕያ የወያኔእና የኢዲዩን የኦነግና የወያኔን የደቡብና የኦጋዴን አንዱ ከአንዱ ጋር ግንባሩን እየቀየረ „መዋጋት“ የምንረዳው „አገሪቱን ለመግዛት ሕዝቡን ለመምራት መሬቱን ለመያዝ በትረ-መንግሥቱን ለመጨበጥ ሠራዊቱን ፓሊሱንና ፍርድ ቤቱን እሥር – ቤቱን ለመቆጣጠርና ለማዘዝ …እኔ ብቻ ታሪካዊ ኃላፊነት አለኝ ይገባኛል“ ከሚለው ፍልስፍና የመነጨ ነው። ችግራችን እሱ ነው።መኳንንቱም፣ መሣፍንቱም ይህን ብለው ይህ ከአልሆነ ብለው ተናንቀዋል። ነገሥታቶችም። ይህን የሚቃወምና የሚተች ሌላም መፍትሔም አለ እኮ እስቲ እሱን እናሰላስል የሚል ሰው ወይ „ይደመሰሳል“ ወይ „ ይቀጣል“ ወይም አገሩን ጥሎ „እንዲሰደድ“ ይገረጋል። ወይም ደግሞ አፉን በጠበንጃ ፍረሃት ይዞ እንዲቀመጥ ይገደዳል። አልፎም የስም ማጥፋት ዘመቻ ይወርድበታል።ነገሮችን ለመረዳት፣ ስለ እብሪተኛው ቄሣር ስለኔሮም ያነሳነው ለዚህ ነው። እሱን ብቻ አይደለም። ስለ እባብም አንስተናል። ስለ ሰይጣናና ስለ ሳጥናኤል ተርከናል። የፕላቶና የሶቅራጥስንም ምክሮች ጎትተን የጠቆምነውም ከገባንበት ለመውጣት ማሰብ ማጥናት ማመዛዘን አለብን የሚለውን ጥበብ ለመጠቆም ነው። ሰይጣን አለ ወይ ? ብለን እራሳችንን ጠይቀናል። ለመሆኑ እንደሚባለው እኛ ጥቁሮቹ ተረግመናል? ወይስ ነጮች ተመርቀዋል? የሚለውንም ጥያቄ ሰንዝረናል። ጥፋተኛው ገዢው መደብ ብቻ ሳይሆን ሰዎችም „ጠንካራ ክንድ“ የማየት ድክመ bmH8b