ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 54

አዎን አለ-ሌላው ጣልቃ ገብቶ። እንዴት? የሚባለው ጥያቄ ተወረወረ። „…ዘለዓለማዊ አስተሳሰብ፣ጊዜ የማይሽረውና ጊዜ የማይቀይረው አመለካከት፣ የለም። እራሱ የሳይንስ ምርምር እንኳን ቢሆን ከተወሰነ አመት በሁዋላ የሚቀየር የሚለወጥ የሚሻሻል ነው። ከዚያም በላይ ሁላችንም ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ -ሕይወት ገደብ አላት- ከዚህቺ ዓለም ሁላችንም ተሰናብተን የምንሄድ ነን። የበርሊን ግንብ ይፈርሳል።ሶቪየት ሕብረት ይወድቃል።ኮሚኒስቶች ሥልጣን በሕዝብ ድጋፍ እንደወጡት በሕዝብ አመጽ አንድ ቀን ወድቀው ሥልጣኑን ያስረክባሉ ብሎ የገመተ ሰው አልነበረም። ግን እንደምናየው እነሱም ሄደዋል።…“ አለች።