ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 51

አንድ ወጥት ወንድ ልጅ እግሩን አጣምሮ አባቱ አጠገብ ቁጭ ብሎ ይህን ሁሉ ጉድ በሚችለው አማርኛ ለመረዳት ይሞክራል። ከእሱ አጠገብ የግሪክ ሐውልቶች አሉ። ግድግዳው ላይ የንግሥት ሳባ ጉዞ ግሩም ተደርጎ ተስሎ ተሰቅሎአል። በሁዋላ ስሰማ በሩ ላይ ከተቀበሉኝ ሴቶች ውስጥ አንደኛዋ የእሱ የተቀመጠው ጎልማሣ እህት ስድሳኛውን አመቱን ያኔ ያከበረው ጓደኛዬ ልጅ/ልጆች ናቸው። እኛም ያኔ በእነሱ ዕድሜ በነበርንበት ዘመን- በስድሳውና በሳባው አመተ ምህርት „ያዙኝ ልቀቁኝ“ እንል ነበር። እነሱ ግን ረጋ ያሉ ናቸው።“ እያልኩ እራሴንም ትውልዴን እታዘባለሁ። ትንሽ ቆይተው „…ሁላችሁም ጥቁር ናችሁ። ለምንድነው እኔ ትግሬ እኔ ኦሮሞ አፋር ሱማሌ ሓማሴን እያላችሁ የምትጣሉት ?“ ብለው ሰውን ሁሉ ይጠይቃሉ። ለዚህ መልስ የለም። ዝም ብሎ ታለፈ። ሌላም አርዕስት ተነሳ። „የፕሮሌታሪያን ያኔእንደሚባለው የላብ አደሩ/ወዝ አደሩ አምባገነን መንግሥት…“ምን ታይቶን ነው ይህን ሐሳብ ርዕዮተ ዓለም የተቀበልነው? አለ አንደኛው። ቤቱ ሳቀ። -ዱሮ ይህ ቢሆን መግቢያም ቦታ የለም።…ትወገዛለህ! ትኮነናለህ!ለእነሱ -ለወጣቱ ትውልድ እንደዚህ ዓይነቱ ፖለቲካ ምናቸውም አይደለም። „ለመሆኑ ለዚህ አመለካከት ለመሞት ዝግጁ ነህ ወይ ? ተብለው ቢጠየቁ …ምን ~ 51 ~