ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 5

ሁሉም ባዶ እጁን ነው የወጣው። ንጉሣዊ ቤተሰቦች -ይህ አያነጋግርም- ምንም ያተረፉት ነገር የለም። ..አላተረፉም። መሣፍንቱና መኳንንቱ እንደዚሁ ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል። ያ የሚፈራውና ግርማ ሞገስ የነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊትና ፖሊስም በመጨረሻው ወይ ሞተዋል ወይ ተበትኖአል። ደርግ ከአለ ኮ.መንግሥቱና ከፍቅረ ሥላሴ ድርስቶች ሌላ ምንም ከእነሱ የተረፈና የቀረ ነገር የለም።ጨፍረው ጨፍረው የት ደረሱ? ስደት እሥራት ሞት። ብዙ የሚነገርለትና የሚወደስለት የተማሪው እንቅስቃሴ እና ከእነሱ አብራክ የወጡት የፖለቲካ ደርጅቶች -እጭኣት ኢህአፓ መኢሶን ወዝ ማሌሪድ …ዛሬ የት ናቸው? ከጥቂት አመታት በፊት ጊዜው ለኢትዮጵያ „ነጻ-አውጪዎች ነው“ ተብሎ በሰፊው ተነግሮ አላስቀምጥ አላስቆም ብለውን ነበር። ግን እነ ኦነግ እና እነ የደቡብ ሕዝቦች መላ አማራና አማራጭ ኃይሎች…እራሳቸው አንዳንዶቹ የእህዴግ ተከታዮች ጭምር አሁን የት ናቸው? የት ነው ያሉት? ሻብዕያና ጀበሃ ሕዝባዊ ወያኔና ኦጋዴን አፋርና …እነሱ አሸናፊ ሁነው ወጡ ሊባል ይችላል። ግን ምን አዲስ ነገር ለአገሪቱ ለሕዝቡ ለተከታዮቻቸው አመጡ? ምን ያህል ሰው ነው እነሱን አሁን የሚከተላቸው? ምን ተአምር ሰሩ? በእነሱ የሚያለቅስ የለም? ምናልባት በኢትዮጵያ ውስጥ በተነሳው ትርምስ ያተረፉት ቻይና እና ሕንድ አረቦችና አሰፍስፈው መሬቱዋን ለመግዛት የሚጠብቁ የውጭ ኃይሎችና መንግሥታት ናቸው ልንል እንችላለን። አሁን ጥሩ ጨዋታ ተጀመረ! ~5~