ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 45

ጊዜና ሰው የአዛውንት ጉባዔ ለማሳረጊያ ከምግብ በሁዋላ በዚያ በበጋ ወራት ወደ ማምሻው ላይ ከቡና ጋር የቀረበው ጣፋጩ ዲሰርት መንጋጋን ብቻ ሳይሆን ዓይንንም ከሩቁ ማርኮ ምራቅ የሚያስውጥ ነው። ማነው ኢትዮጵያ ዲሰርት የላትም? እሱንም አታውቅም የምለውን ጥያቄ አንዴ ያነሳው? ይህን ቢያይ እሱ ደንግጦ አፉን ይይዛል። ከዓሣና ከጎድን ጥብስ ከዶሮ መረቅና ከቀይ ወጥ ከአልጫና ከአታክልት ከምስርና ከሽሮ ከክ ወጥና ከሽቡራ ዓሣ ከክትፎና ከቁርጥ ከአይብና ጎመን ከፍርፍርና… ከቅልጥም ከፍትፍትና – የአገራችን ምግብ ከቻይና ቀጥሎ በዓይነቱም በብዛቱም ሁለተኛ ነው ይባላል – የግሪክ አማልክቶች ታላቁ የመጀመሪያው ደራሲ ሆሜር እነደ ጻፈው ግሩም ምግብ ንጹህ አየር ደስ የሚል አስተናግዶ ሲያምራቸው ወደ ኢትዮጵያ ይወርዱ ነበር ይላል – ከእነዚህ ሁሉ ግሩም ጠረጴዛው ላይ ከተዘረጉት የባህል ምግቦችና የቀቃይ ጥበቦች በሁዋላ ለማሳረጊያ ከቡና ጋር የቀረብልን ዲሰርት ጣፋጩ የነጮች አይስ ክሬም አልነበረም። ~ 45 ~