ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 44

ነገሩ አጸያፊ ነገር ይመስላል። አክ የተባለበትንና የተተፋበትን ቆሻሻ ወኃን ወይም ደግሞ የሽንት ቤት መጸዳጃ ውሃን ሺህ ጊዜ ተጣርቶ ተመልሶ ቢመጣ እሱን እንደገና ማን ይጠቀመዋል? …ይዘገንናል። ሳይንሱ ግን ሌላ ነው።1የአባይን ውሃ የምድቴረኒያን ባህር ፈሶ ከመግባቱ በፊት አሥር ጊዜ መልሶ መላልሶ በኢትዮጵያም በሱዳንም በግብጽም አገር መጠቀም ይቻላል። ጋዜጣው ስለዚህ እንደዚህ ዓይነቱ የአጠቃቀም ዘዴ አያነሳም። ጋዜጣው በአጠቃላይ ያተኮረው በዓለም ሕግ መሠረት በ1997 እአእ የወጣ ግልጽ ያልሆነ በሠላሣ መንግሥታት ብቻ የተደገፈ የተባበሩት መንግሥታት ደንብ አለ- በዚያ መሰረት የኢትዮጵያና የግብጽ መጪው ውዝግብ የት ያደርሳል ?ብሎ ይጠይቃል። እግረ መንገዱንም ስለ ኮንጎ ወንዝ ያነሳል። እዚያም የጎረቤት አገሮች በጋራ አንድ ግድብ ገድበው የኤሌትሪክ መብራት ኃይል አመንጨተው በጋራ ለመጠቀም እንደፈለጉም ይጠቅሳል። በተጋሊጦሹ የኮንጎ መንግሥት ይህን ሓሳብ በጥርጣሬ ዓይን ያየዋል ብሎ ዘገባውን ጸሓፊው ይዘጋል። የዞረበት ዓለም! ትላንት ለጥራት የተላከው ወሃ ነገውን ተጣርቶ ለመጠጥ ወይም ለወጥ ሥራ በሁለተኛው ቀን አይቀርብም። የተጣራው ውሃ በክረምት ከወረደው ዝናብና ከበረዶ ወሃ ጋር ተደባልቆ መሬት ውስጥ ከተቀበረውም ንጸህ ወሃ ጋር ተቀላቆሎ ከአሥር አመትበ ሁዋላ በደንብ ጸድቶ አገልግሎትለላ ይውላል። እራሱን የቻለ ሳይንስና ገንዘብ ጠሚያመጣ ሐብት ነው። ወሃ ለአወቀበት ሕዝብ አይደፋም። ጅረትም ዝም ብሎ አይፈስም። ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 ~ 44 ~