ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 40

አባይ :- ኢትዮጵያና ግብጽ አንድ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚፈሱትን ወንዞች ሌሎች የጎረቤት አገር ከመድረሳቸው በፊት መገደብ ይችላል ? ወይስ አይችልም ? በሚል አርዕስቱ ሥር „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ የተባለው የደቡብ ጀርመኑ ዕለታዊ ጋዜጣ አንድ ሙሉ ገጹን ለዚሁ ወደፊት ዓለምን ሳያበጣብጥ አይቀርም ተብሎ ለሚገመተው ጉዳይ ጊዜውን ወስዶ ቅጠሉን ለግሶ የሚከተለውን አስተያየት አምዱ ላይ አሥፍሮአል። ሌሎቹ የአፍሪካና የሰሜን አሜሪካ ጋዜጣዎች ስለ አፍሪካ ምን እንደጻፉ መለስ ብለን ዝርዝር ሁኔታ ውስጥ ሳንገባ ይህኛውን አርዕስት ብቻ ለመመልከት ወስነናል።ጉዳዩ አሳሳቢና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። መጪው ጦርነት እንደ ዘጠናዎቹ ዓ.ም “በዘርና በጎሣ….በብሔር/ብሔረሰብ” ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ጠበብቶች ተስማምተው እዚህ እንደሚሉት መጪው ጦርነት በሕይወት ጥያቄ ላይ ያተኮረ ነው። ~ 40 ~