ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 36

ጠንካራ ክንድና ነጻነት ሰው ምን እንደሚፈልግ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚያ ሲሉት በዚህ ይታለል። ያን ሲያቀብሉት እጁ ላይ ያለውን ጥሎ እንደ ህጻን ልጅ ያኛው ያምረዋል። ይህን ሲሰጡት ጨምር- አልበቃኝም ይላል።ሲበዛበት ደግሞ ቋቅ ሲለው ይ… ሰው አስቸጋሪ ነው። እንደ ሰው አስቸጋሪ ፍጡር የለም። እሩቅ ቦታ ሳንደርስ በቅርቡ በተካሄደው በቱርኩ ኤርድዋን በሩሲያው ፑቲን በእነሱ እርምጃ ያልተደሰተ በተቃራኒው ያልተበሳጨ ሰው የለም። የግብጹ ሙርሲና ፊልድ ማርሻል አዚዚ አሉ። ሁለተኛውን ትተን የመጀመሪያዎቹን እንውሰድ። „ፑቲንን ለሩሲያ ኤርድዋን ለቱርክ እግዚአብሔር መርቆ የሰጣቸው መሪዎች ናቸው!“ ብዙ ሰዎች ይላሉ። በተለይ ቪላዲሚር ፑቲን „ትልቅ ቦታ“ በአንዳንድ ኢትዮጵያኖች ዘንድ አላቸው። ከልብ ይሁን ከምኞት፣ እነሱን ከገቡበት የሚያወጣቸው ሰው አጥተው ይሁን ወይም ተመሳሳይ ሰው ናፍቀው፣ወይም ከአለፉት ታሪክ ተነስተው -ሁሉም በየፊናው የሚሰጠው አስተያየት የተለያየ ነው- ምኑንም ከመገመት በላይ ይህ ~ 36 ~