ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 28

አንደኛው የፕላቶ ተማሪ የታላቁ እስክንድር አስተማሪ የሆነው አርስጣጥለስ የነደፈው ኢምፔሪካል ጥናት ነው። ዘመናዊ ሳይንስም አሁን የሚከተለው ሁለተኛው መንገድ ፕላቶና አስተማሪው ሶቅራጠስ የሚሉት የሰው ልጅ እራሱን ከፍ አድርጎ አስተካክሎ ሊደርስባቸው የሚፈልጋቸው የመኖር ዘይቤ ናቸው። ይህን ለማስረዳት ፕላቶ ሙዚቃንና የከዋክብቶች አቀማመጥን እንደ ምሳሌ ይወስዳል። መንፈስን የሚያድሰው እንደ የሂሳብ ትምህርት ሥርዓት የተቀነባበረው የሙዚቃ ድርሰትና ማታ ማታ አንገታችንን ከፍ አድረግን ሰማዩን ስንመለከት የምናያቸው የክዋክብቶች ቅንብር ቁንጅናቸው -ሓርሞኒ ይለዋል- አቀማመጥ ናቸው። ፕላቶ ይህን ነገር በሌላ ምሳሌ ለማስረዳት ብዙ ፈረሶች በአንድነት የሚጎትቱን ሠረገላም አድርጎ ያቀርበዋል። ፈረሶቹ በአንድነት ካአልረገጡና ሠረገላውን በሶምሶማቸው አስተካክለው ከአልሳቡት ወይ ሠረገላውን ይገለበጡታል ወይም ይሰብሩታል ወይም ደግሞ ከቆሙበት ፈቀቅ አይሉም። ይህ „ይሰበራል“ የሚባለውን ነገር ደግሞ እንደ ፕላቶ እንደ እሱ የሚያስፈራው ነገር የለም። አንድ ሕብረተሰብ ተንኮታኩቶ ከወደቀ ደግሞ ከዚያ በሁዋላ ምን እንደሚመጣ? ማን እንደሚተካው? ምንም የሚታወቅ ነገር ስለ ሌለ አትንቀጅቀጁ ተማሪዎቹን ይላል ። ፕላቶ “አብዮት” የሚባላውን ነገር ከዚህ ተነስቶ አይወደውም። ይህም የክፋት ሥራ ከየት እንደሚመጣ መልስ እንድንፈልግ ይረዳናል። ለምንድነው ሰዎች ክፉ መጥፎ ሥራ የሚሠሩት? ….አውቀው ነው ወይስ ሳያውቁ? እነሱ እራሳቸውን ገደል ለመክተት ፈልገው ነው ወይስ “ጥሩ” ሥራ እየሰራን ነው ብለው በማመናቸው ነው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አንደኛው ፈላስፋ ሶቅራጠስ ጥሩ መልስ የዛሬ ስንት ሸህ አመት መልስ ሲሰጥ „ሳያውቁ ምንም ነገር በአለማወቃቸው መሓይም ~ 28 ~