ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 23

አላቸው ይነገራል። (ii ጥንታዊ ግሪኮች ሰይጣንን እኛ በምናውቀው ዓይነት እነሱ አያውቁትም። „ክፋትን“ ግን ምን እነደሆነ በደንብ አድርገው ያውቃሉ። እንዲያውም „ክፋትን መክቶ የሚከላከል አምላክ/አማልክት“ አለ ይላሉ። ይህ ደግሞ ለምን እኛን የሰው ልጆችን የሚፈታተን ሰይጣን እግዚአብሔር ላከብን? ለምን ሰይጣንን ከእኛ አያርቅም? ለምን እንደዚያ እየተፈራረቁ ሲያስቸግሩን ዝም ብሎ ያያል? እጁን ዘርግቶ ለምን አያድነንም? የሚሉትን አቤቱታዎች ያስነሳል። እናሳጥረው። …ሰው ሰይጣን ነው። ሰይጣንም ሰው ነው። ይህ አባባል ዕውነት ይሆን? ወይስ ሰይጣን/ሰይጣኖች በአየር ላይ ከንፈው/ከንፎ ሳይታሰብ ሰውን ወይም አንድን አገር አንድን ሕዝብ የሚያሰቃዩ መናፍስት/መናፍሰቶች ናቸው? ይህንና ይህን የመሰሉ ጥያቄዎች…ከቃዬልና አቤል ከዳዊት እና ከጎሊያድ ከዩሊዮስ ቄሣር እስከ ኔሮ እስከ ካሊ ጉላና እስከ ከኢቫን ጨፍጫፊው ከስታሊን እሰከ ሒትለር ያሉትን ሰዎች የምንረዳውና የምንመልሰው አእምሮአችንን ከፍተን ነገሮችን በትክክል ለማየት ስንችል ነው። ሕጻናትን የሚዳፈሩ የከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሶች አሉ። በኮሙንዝም ስም እነ ኪም ኢል ሱንግ ሥልጣን ላይ ወጥተው ውርርሱን ወደ ንጉሣዊ አገዛዝ ወደ አልጋ ወራሾች ሥርዓት ቀይረውታል። ትላንት ጫካ አንድ ላይ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ጠላት ሁነዋል። ትላንት „ዲሞክራሲና እኩልነት“ ይል የነበረው ሰው ዛሬ ጊዜው አይደለም ይላል። „…ሰው ሰይጣን ነው ሰይጣንም ሰው ነው“ ~ 23 ~