ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 22

ብለውም ይፈሩ ነበር። ከዚያ በፊትስ ምን ነበር? የፈርዖኖቹ ታሪክ እንደሚለው ቀደም ሲል አማልክቶቹና የሰው ልጆች በንፋሱ ንጉሥ ሳይለያዩ አንድ ላይ በዚህች ምድር ላይ ተደበላልቀው ይኖሩ ነበር። በዚያም ዘመን የሰው ልጆች እየረበሹ የአምልክቶቹን ጸጥታ ነስተው ረብሻ እዚህም እዚም ተነስቶ ግርግር ጩኸትን ትርምስ በአገሪቱ ነግሦም ነበር። አማልክቶቹም ተቸግረው ሰዎችን ዝም ለማሰኘት እነሱን እያሳደዱ ይቀጡ በጦራቸውም ይዋጉ ነበር። ለጃፓኖች ሥርዓቱንና ደንቡን በሰው ልጆች መካከል ሳያዳለ እየዘረጋ እንዲፈርድም እየፈረደም እንዲገዛ የጸሓይ ልጅ ንጉሥ ሁኖ እነሱን እየተቆጣና እየቀጣ እንዲያስተዳድር ከሰማይ ለእነሱ -ታሪካቸው እንደሚለው- ተልኮላቸዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ ሲወርድ ሲዋረድ ንጉሥ አኩሂቶ ላይ ደርሶአል። በግሪክ አገር የአማልክቶች ጦርነት እኔ እበልጥ እኔ እሻል በሚባል ፉክክር ገብተው ሶይስ የተባለው የአማልክቶች አለቃ (ተወልዶ) እስከሚነሳ ድረስ በመካከላቸው ረብሻ ነግሶ በጦር እንደተፈላለጉ ጊዜውን ገፍተው ነበር። ሶይስ ከመምጣቱ በፊት በምድርም በሰማይም ላይ ይህ ነው የማያባል ረብሻና ትርምስ ብቻ ሳይሆን ግዲያና ፍጅት ጋብቻና ቅሚያ ድፍረትና አመንዝራነት በአማልክት ልጆችና በወላጆቻቸው በወንድምና በእህት (እንደ ሰው ልጆች እነሱም ይጋቡና ይዋለዱ ነበር) ዝብርቅርቁ የወጣ የተጨማለቀ ልማድ በመካከላቸው ሰፍኖ አንዱ ሌላውን ጭምር ይበላውም ነበር። (i ሶይስ ብቻ አፈ-ታሪኩ እንደሚለው እናቱ አንድ አማልክት ሊደርሱበት ከማይችሉበት ዋሻ ውስጥ ደብቃው እሱ ከሞት ይተርፋል። አድጎ ጉልበት ገዝቶ ከዋሻው ሲወጣ ጦርነት በአባቱና በእህቶቹ በወንድሞቹም ላይ ይከፋታል። አሽናፊ ሁኖ ወጥቶ ድል አድራጊው ሶይስ- አፈ ታሪካቸው እንደሚለው- በቂም በቀል አባቱንም እህቶቹንም ሳያጠፋ ምህረት አድርጎላቸው አባቱን በግዞት የእንድ ደሴት ንጉሥ እህቶቹንና ከሞት የተረፉትን ወንድሞቹን ደግሞ የባህር ንጉሥ የውቅያኖስ ንጉሥ የፍቅር የጦርነት የሐዘን …ንጉሥ እያለና እየሾመ እሱ የሰማይ ንጉሥ ሁኖ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሰማይና ምድርን ይገዛል። የሥልጣን ክፍፍል በ b&