ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 20

ለምንድነው ሌሎቹ ሲጌጡ የተቀሩት ራቁታቸውን አሁን ድረስ የሚሄዱት? ለምንድነው ከልብስም በዘመናዊ ልብስ አጊጦ ተኳኩሎ መውጣት በአውሮፓ እየተስፋፋ የሄደው? ለምንድነው በሌላው አካባቢ መሸፋፈን የነገሰው? ለምንድነው ሌሎቹ ከአፈርና ከጭቃ ቤት ሲሰሩ የድንጋይ ቤቶች ጥበብ ቪላና ትላልቅ ቤተ-መንግሥት መሥራት ሌላ አካባቢ የተጀመረው? ለምንድነው የሮምና የፓሪስ የበረሊንና የሊሳቦን ሕንጻዎችና ቪላዎች ከአፍሪካውያኖቹ በአሰራራቸው በውበታቸው በአቀማመጣቸው የሚያማመምሩት? ለምንድነው ነጮች ተከባብረው ተቻችለው አብረው ተስማምተው ሲኖሩ አፍሪካ እርስ በእራሱ የሚጣበሰው? ቆየት ብለን ወደ በሁዋላ እንደምናየው ገበሬው ቃዬል ከብት አርቢ ወንድሙን አቤልን „በቅናት“ ተነሳስቶ ደብድቦት ይገድለዋል። ትንሽ ዘግይቶ በሰው ልጆች ሥራ -አሁንም መጽሓፉ እንደሚለውእግዚአብሔር አዝኖ የወሃ ጥፋት ይከተላል። በአባቱ እርቃንነት ያላገጠ ልጁን ኖህ ካምን ይረግመዋል። ሰዶምና ጎሞራ በእሳት ይቃጠላል። የባቢሎን ግንብ ይፈርሳል። „ከእንግዲህ አላጠፋችሁም“ የሚለው የመጀመሪያው ውልና ቃል-ኪዳን ቀስተ-ደመና በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል ይደረጋል። በሁዋላ እንደምናውቀው ብዙ ፈላስፋዎች ይህን ሓሳብ መሠረት አድርገው „ሶሻል ኮንትራት“ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተቻችለውና ተከባብረው በጋራ የሚኖሩበት „የጋራ ቃል-ኪዳን“ ብለው የፖለቲካ ቲዎሪአቸውን ነድፈዋል። ይህ እንደዚህ አሁን እንደ ዋዛና ፈዛዛ እዚህ የሚተረከው ታሪክ አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ወንድሙን ወይም ጎረቤቱን ጠላቱንም ቢሆን